የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

ኢትዮጵያ ያጣችውን የባሕር በር ለማስመለስ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት የሚደነቁ ናቸው

Oct 12, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሀዋሳ ፤ ጥቅምት 1 /2019 (ኢዜአ):-ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚና በሴራ ያጣችውን የባሕር በር ለማስመለስ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት የሚደነቁ መሆናቸውን ምሁራን ገለጹ፡፡

የባሕር በርን በሰላማዊ መንገድ ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለው ጥረት የዜጎች እና የምሁራን የነቃ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ወደ ባሕር የሚያወጣ መውጫ ከሌላቸው ሀገራት መካከል በሕዝብ ብዛት ትልቋ ሀገር ስትሆን፣ በፍጥነት እያደገ የሚሄደውን የሕዝብ ቁጥሯንና የኢኮኖሚ ፍላጎቷን ለማስተናገድ ለሀገሪቱ የቀጥታ የባሕር በር የማግኘት አስፈላጊነት አከራካሪ አይደለም።

ሀገሪቱ በየዓመቱ ለወደብ ኪራይና ለሎጂስቲክስ አገልግሎት የምታወጣው በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር የውጭ ምንዛሪ፣ በሀገር ውስጥ ልማትና በምግብ ዋስትና ላይ መዋል የሚችለውን ሀብት የሚሻማ ነው።

በመሆኑም በሰጥቶ መቀበል መርህ የተረጋጋና አስተማማኝ የባሕር በር ባለቤት መሆን የሀገሪቱን የንግድ ሚዛን ከማስተካከሉም በላይ፣ የኢንዱስትሪና የንግድ ምርቶችን በዝቅተኛ ወጪ ወደ ዓለም አቀፍ ገበያ ለማቅረብ አቅምን ይፈጥራል።

የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንም የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት በሕጋዊና በሰጥቶ መቀበል መርህ ለማረጋገጥ የተጀመረው ዲፕሎማሲያዊ ጥረት የዜጎችን እና የምሁራን የነቃ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።

ኢዜአ በጉዳዩ ዙሪያ ካነጋገራቸው የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካ ሳይንስ ምሁራን መካከል፣ በዩኒቨርሲቲው የምርምርና ትብብር ምክትል ፕሬዚዳንት ታፈሰ ማቲዮስ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ የባሕር በር ጉዳይ ለኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ምሰሶ ብቻ ሳይሆን የብሔራዊ ጥቅም እና የህልውና ጉዳይ ነው።

ይህን እውነታ በካደ መልኩ ግብፅ የታላቁ የሕዳሴ ግድብ እንዳይሠራ የነበራትን የማደናቀፍ ጥረት፣ አሁን ደግሞ በባሕር በር ማስመለስ ጉዳይ ላይ አጠናክራ ቀጥላለች ብለዋል።

ይህም የአባይን ወንዝ በብቸኝነት ከመጠቀም ፍላጎት የመነጨና የኢትዮጵያን ዕድገት ለመግታት ያለመ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ይህንን ተፅዕኖ ለመቀልበስ የተጀመረውን የዲፕሎማሲ ስራ እውን ለማድረግ፣ የዜጎችን የነቃ ተሳትፎና በተለይም የምሁራንን ሙያዊ እገዛ እንደሚጠይቅ አስረድተዋል።

የፖለቲካ ሳይንስና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ አቶ ዳያሞ ዳሌ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በታሪክ አጋጣሚና በሴራ ያጣችውን የባሕር በር ለማስመለስ እየተከናወኑ ያሉ ዘርፈ ብዙ ተግባራት የሚደነቁ ናቸው ብለዋል።

ይህን ሕጋዊና ታሪካዊ መብት የማረጋገጥ ጉዳይ አገራዊ አጀንዳ መሆኑንም ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ አሁን ላይ የገነባችው ጠንካራ የኢኮኖሚ አቅምና ከታላቁ የሕዳሴ ግድብ መመረቅ ጋር ተያይዞ ጎረቤት ሀገራትን በኤሌክትሪክ ኃይል መሠረተ ልማት የማስተሳሰር ሥራ በቀጠናው ያላትን ተቀባይነት አሳድጎታል ያሉት አቶ ዳያሞ፤ ይህንን ተጨባጭ እውነት የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብም በሂደት እየተረዳውና ድጋፉን እያሳየ መምጣቱን አስረድተዋል።

ኢትዮጵያ በጋራ ተጠቃሚነትና ዲፕሎማሲያዊ በሆነ መንገድ የባሕር በር ባለቤትነቷን የማሳካት ሂደት ሕግን ያከበረና ፍትሐዊነትን መሠረት ያደረገ መሆኑንም አብራርተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅ ላይ ትኩረት ተሰጥቷል

መቱ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):- በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ገቢና የአካባቢውን አምራቾች ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅና...

Sep 23, 2026

በክልሉ ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በማዋል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠና...

Sep 18, 2026

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026

በክልሉ ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት ተደርጓል

ወላይታ ሶዶ፤ ጳጉሜን 4/2018 (ኢዜአ) ፦በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ለዘመን መለወጫ በዓል የምርት አቅርቦት እጥረት እንዳይከሰት በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ን...

Sep 10, 2026