የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

በሲዳማ ክልል ከ34 ሺህ 500 ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ የደረሰ ምርት እየተሰበሰበ ነው

Oct 20, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ሀዋሳ፤ ጥቅምት 9/2019 (ኢዜአ)፦በሲዳማ ክልል ከ34 ሺህ 500 ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ የደረሰ ምርት በጥራት የመሰብሰብ ሥራ መጀመሩን የክልሉ ቡና፣ ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን አስታወቀ።

በክልሉ የሚገኙ ቡና ላኪ አርሶ አደሮችና ቡና የሚያዘጋጁ ኢንዱስትሪዎች በበኩላቸው ዘንድሮ ቡና ፈጥኖ በመድረሱ ምርት የማሰባሰቡ ሥራ መጀመራቸውን ገልጸዋል፡፡


የሲዳማ ክልል ቡና፣ ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ መስፍን ቃሬ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በክልሉ ጥራት ያለው ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ተከናውኗል፡፡

በክልሉ ለማዕከላዊ ገበያ ከሚቀርበው ቡና ከ89 ከመቶ በላይ የሚሆነው የታጠበ በመሆኑ የታጠበ ቡና የሚያዘጋጁ ከ472 በላይ ኢንዱስትሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት አድርገው ወደ ሥራ ገብተዋል ብለዋል፡፡

በክልሉ የሚሰበሰበው የቡና ምርት ጥራቱን የጠበቀ እንዲሆን ከለቀማ ጀምሮ የቡና ማድረቂያ ቦታዎችን የማስተካከል፣ የማጠቢያ ገንዳዎችንና መጋዘኖችን የማዘጋጀት ሥራ በትኩረት መከናወኑን ጠቅሰዋል፡፡

በክልሉ ከ198 ሺህ ቶን በላይ እሸት ቡና በመሰብሰብ ከ34 ሺህ 500 ቶን በላይ የታጠበና ያልታጠበ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል።


ዘንድሮ ቡና ቀድሞ በመድረሱ ምርት የመሰብሰብ ሂደቱ ቀደም ብሎ መጀመሩን ገልጸው፣ እስካሁንም 25 ከመቶ በላይ የሚሆን የቡና ምርት ተሰብስቧል ብለዋል።

የቡና ጥራት ለማስጠበቅ ከሚከናወኑ ተግባራት በተጨማሪ ምርቱን በአግባቡ ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብና ህገ ወጥ ንግድን ለመከላከል በግብረ ሃይል የታገዘ ክትትል እየተደረገ መሆኑንም አመልክተዋል፡

በክልሉ ከሚመረተው ቡና 20 ከመቶው ባለ ልዩ ጣዕም ቡና እንዲሆን በልማቱ ለሚሳተፉ ከ2 ሺህ በላይ አርሶ አደሮች ተገቢው ስልጠና ተሰጥቶ ወደ ሥራ መገባቱንም ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

ከአርሶ አደሮቹ በተጨማሪ ባለሃብቶችና ማህበራትም በኢንዱስትሪዎቻቸው የባለልዩ ጣዕም ቡና እንዲያዘጋጁ በማድረግ የዓለም ገበያ ፍላጎትን ያሟላ ምርት ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ዳይሬክተሩ አክለው እንደገለጹት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተጀመረው እሸት ቡና የመሰብሰብ ሂደት እስከ መጪው ታህሳስ ወር በሁሉም አካባቢዎች ይጠናቀቃል፡፡


በክልሉ ሸበዲኖ ወረዳ ፉራ ቀበሌ ቡና ላኪ አርሶ አደር አቶ ዮሴፍ ተፈሪ በ4 ነጥብ 6 ሄክታር መሬታቸው ላይ ካለሙት ቡና እስካሁን ከ270 ኩንታል በላይ ምርት ሰብስበው ጥራቱን በጠበቀ መልኩ እያዘጋጁ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ዘንድሮ ከ400 ኩንታል በላይ ቡና ለዓለም ገበያ ለማቅረብ ዕቅድ እንዳላቸው ገልጸው፣ ከማሳ የቀላ ቡና ብቻ በመልቀምና በአግባቡ በማድረቅ ጥራቱን ለመጠበቅ እየሰሩ መሆኑን አስታውቀዋል፡


በሸበዲኖ ወረዳ የበሹራ ቦና የቡና ማዘጋጃ ኢንዱስትሪ ሥራ አስኪያጅ አቶ ሙላቱ ሙርጋቶ በበኩላቸው እንዳሉት፤ ከ390 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ እሸት ቡና ከአርሶ አደሩ በመግዛት በጥራት የማዘጋጀት ሥራ እያከናወኑ ይገኛሉ።

በኢንዱስትሪው የሚዘጋጀው ቡና ጥራት ያለውና በዓለም ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆን አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጎ ወደስራ መገባቱን ጠቁመው፣ ዘንድሮ ምርቱ ከአምና የተሻለ ነው ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ምክር ቤቱ ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል የብድር ስምምነትን አፀደቀ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚው...

Oct 14, 2026

በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅ ላይ ትኩረት ተሰጥቷል

መቱ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):- በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ገቢና የአካባቢውን አምራቾች ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅና...

Sep 23, 2026

በክልሉ ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በማዋል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠና...

Sep 18, 2026

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026