🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ጥቅምት 10/2019 (ኢዜአ)፦በግብርና ዘርፍ የተደረጉ የህግና የፖሊሲ ማሻሻያዎች ሴቶች በዘርፉ ያላቸው ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲያድግ ዕድል መፍጠሩን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ።
3ኛው ሴት የሆርቲካልቸር ስራ ፈጣሪዎች ጉባኤ "ከተሳታፊነት ወደ መሪነት" በሚል መሪ ሀሳብ ተካሒዷል።

በግብርና ሚኒስቴር የሚኒስትር ዴኤታ ተወካይ አቶ አበራ ለማ እንደገለፁት፤ ግብርና በኢትዮጵያ ትልቁ የኢኮኖሚ ማግኛ ምንጭ ነው።
መንግስት የሆርቲካልቸር የግብርና ዘርፍ እንዲያድግና ምርትና ምርታማነቱ እንዲጨምር በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
ዘርፉ ለጠቅላላ ዓመታዊ ምርት፣ ለግብአት አቅርቦትና ለውጪ ምንዛሪ ግኝት ጉልህ አስተዋፅኦ እያበረከተ ስለመሆኑም አንስተዋል።በግብርና ዘርፍ የሴቶችን የነቃ ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተለያዩ የአሰራር ስርዓት ተግባራዊ ተደርጓል ነው ያሉት።
ለአብነትም የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ አንዱ ሲሆን፤ አዋጁ ሴቶች የባለቤትነት መብታቸው እንዲጠበቅ በማስቻል ምርታማነታቸው እንዲጨምር እድል ፈጥሯል።

በተጨማሪም የግብርና ዘርፍ የስርዓተ ጾታ እኩልነት፣ የግብርና ኤክስቴንሽን፣ የሜካናይዜሽንና ብሔራዊ የሆርቲካልቸር ስትራቴጂዎች ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል።
እነዚህ የተሻሻሉ የአሰራር ስርዓቶች በዘርፉ የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት እንዲጨምር ያደረጉ መሆኑን የገለጹ ሲሆን፤ በሆርቲካልቸር ዘርፍ ብቻ ከ80 በመቶ በላይ ሴቶች በተለያዩ መስኮች እንዲሳተፉ እድል ፈጥሯል።
ጉባኤው የዘርፉን ምርታማነት ለመጨመር፣ የሃገራትን ልምድና ተሞክሮ ለመቅሰምና የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን ለመፍታት ዓይነተኛ ሚና አለው ብለዋል።

የጠቅላይ ፍርድ ቤት የቀድሞ ፕሬዝዳንት መዓዛ አሸናፊ፤ በሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ዙሪያ ልምዳቸውን ለተሳታፊዎች አጋርተዋል።
በዚህም የኢትዮጵያ እናቶች ቤተሰብን ከመምራት ጀምሮ ሃላፊነትን በአግባቡ የመወጣት ልዩ ብቃት እንዳላቸው ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ህገ መንግስት ለሴቶች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ጠንካራ መሰረት መጣሉን ጠቁመው፤ ሴቶች በሁሉም ዘርፍ ያላቸውን እድል ለማስፋት ዓይነተኛ ሚና አለው ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት በሃገሪቱ በተለያዩ መስኮች የተሰማሩ ሴቶች ስኬታማ እየሆኑ መምጣታቸውን ገልጸው፤ ሴቶችን በሁሉም ዘርፍ ማሰማራት ውጤቱ የላቀ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
በግብርና ዘርፍ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተደረገ ያለው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን በመግለጽ፤ ሴቶች የተፈጠረላቸውን ምቹ ምህዳር መጠቀም ይጠበቅባቸዋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ለዚህም በሁሉም ዘርፍ የተጀመረው ሴቶችን የማብቃት ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የኢትዮጵያ ሆርቲካልቸር አምራች ማህበር የስርዓተ ጾታ ክፍል ሃላፊ ዮዲት ግርማ በበኩላቸው፤ ማህበሩ በሆርቲካልቸር ዘርፍ የተሰማሩ ሴቶችን መደገፍ ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በተለይም ምርታማነታቸውን መጨመር የሚያስችሉ የግብዓትና የቴክኖሎጂያዊ አሰራሮችን ተደራሽ ማድረግ አንዱና ዋነኛው ስለመሆኑ ነው የገለጹት።
በዘርፉ የተሰማሩ ሴቶች የገበያ እድል የሚያገኙበት አማራጮችን ለማስፋት እየተሰራ ቢሆንም ውጤታማ ለመሆን በጋራ መስራት ወሳኝ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚው...
Oct 14, 2026
መቱ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):- በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ገቢና የአካባቢውን አምራቾች ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅና...
Sep 23, 2026
አሶሳ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በማዋል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠና...
Sep 18, 2026
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026