🔇Unmute
አዲስ አበባ ፤ ጥቅምት 12/2019 (ኢዜአ) ፦የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጓዦች በዲጂታል ፋይናንስ ቀላልና ቀልጣፋ አገልግሎቶች እንዲያገኙ የሚያስችሉ አሰራሮችን አጠናክሮ መቀጠሉን ገለፀ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ዳሽን ባንክና እና ማስተር ካርድ በጋራ የተጓዦች ልዩ ጥቅሞችን የሚያስገኝ የፕላቲንየም ቅድመ ክፍያ ማስተር ካርድ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ተካሂዷል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የሎያሊቲ ፕሮግራም ሀላፊ አቶ ሰለሞን መኮነን በዚሁ ወቅት እንዳት፣ የአዲሱ ካርድ መጀመር አየር መንገዱ በትብብር የሚያቀርባቸውን አገልግሎቶችና የደንበኞችን ታማኝነት ያጠናክራል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ አቪዬሽን ታሪክ ውስጥ ቀዳሚና የኩራት ምንጭ መሆኑን የጠቆሙት ሀላፊው፤ አዲሱ ማስተር ካርድ የአየር መንገዱ አገልግሎት አሰጣጥ ከማዘመን በዘለለ በዲጂታል ክፍያ ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቱን ከፍ ያደርጋል ብለዋል።
አዳዲስ የዲጂታል አማራጮች መተግበራቸው ለተጓዦች ፈጣን፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ልዩ ጥቅሞችና አገልግሎቶች ያስገኛሉ ብለዋል።
አየር መንገዱ ዘመናዊ የክፍያ አማራጮች ተደራሽ ማድረጉ ተጓዦች በዲጂታል ፋይናንስ ቀላልና ቀልጣፋ አገልግሎቶች እንዲያገኙ የሚያስችሉ አሰራሮችን አጠናክሮ መቀጠሉን የሚያሳይ እንደሆነም ተናግረዋል።
የማስተር ካርዱን የሚጠቀሙ ደንበኞች ለአየር መንገድ ትኬት ግዢ፣ ለሆቴል ክፍያ እና ለሌሎች ዓለም አቀፍ የጉዞ ወጪዎች ከጉዞ ጋር የተያያዙ የተለያዩ ቅናሾችን እና ልዩ የጉዞ ጥቅሞች እንዲሁም አገልግሎቶችን እንዲያገኙ ያስችላል ነው ያሉት፡፡

የዳሽን ባንክ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አስፋው አለሙ በበኩላቸው፤ ባንኩ ከኢትዮጵያ አየር መንገድና ከማስተር ካርድ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ማስተር ካርድ ደንበኞች የባንክ አገልግሎትን ከጉዞ ጋር አቆራኝተው በቀላሉ በዲጂታል መንገድ ክፍያዎችን እንዲፈጽሙ ያስችላል ብለዋል።
በሀገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ የዲጂታል አገልግሎቶች ለሚጠቀሙ ደንበኞች ቀጣይነት ያለው እሴት ለመፍጠር ያለመ መሆኑን አመልክተዋል።
የማስተር ካርድ የምስራቅ አፍሪካና የህንድ ውቅያኖስ ደሴቶች ምክትል ፕሬዝዳንት እና ካንትሪ ዳይሬክተር ሚስተር ሼህርያር አሊ፤ ማስተር ካርድ በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር በዓለም አቀፍ ደረጃ ገንዘብ ሳይዙ በካርድ ብቻ ግብይት እንዲፈጸም የሚያስችል ዓለም አቀፍ አውታር መረብ መሆኑን አውስተዋል።
ባንኮችን፣ ነጋዴዎችን እና ደንበኞችን በማገናኘት በዲጂታል መንገድ ክፍያዎችን እንዲፈጸሙ ማድረግ መሆኑን ገልፀው፤ ጉዞ ከዲጂታል አገልግሎት ማቀናጀት እና የደንበኞች ደህንነት በመጠበቅ ምቹና ተደራሽነት ያቀርባል ብለዋል።
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚው...
Oct 14, 2026
መቱ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):- በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ገቢና የአካባቢውን አምራቾች ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅና...
Sep 23, 2026
አሶሳ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በማዋል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠና...
Sep 18, 2026
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026