የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በሩብ ዓመቱ 9 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ገቢ ተሰብስቧል 

Oct 23, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አርባ ምንጭ፤ ጥቅምት 12/2019 (ኢዜአ)፦ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከተለያዩ የገቢ ምንጮች ከ9 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ የገቢዎች ቢሮ ገለጸ።

የቢሮው ሃላፊ አቶ ወንድማገኝ ደግፌ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ ግብር ለሀገር ሰላም ፣ ልማትና ብልጽግና መረጋገጥ ጉልህ ፋይዳ ያለው በመሆኑ በክልሉ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ገቢ ለመሰብሰብ በትኩረት እየተሰራ ነው።

በክልሉ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሦስት ወራት ለመሰብሰብ ከታቀደው 12 ቢሊዮን ብር ውስጥ ከ9 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር በላይ በመሰብሰብ የዕቅዱን 80 በመቶ ማሳካት ተችሏል ነው ያሉት።

በበጀት ዓመቱ ከመደበኛ ገቢ፣ ከማዘጋጃ ቤታዊ እና ከመሬት አገልግሎቶች 48 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑንም አመልክተዋል።

ዕቅዱን ለማሳካት የታክስ መሠረቶችን ከማስፋፋት በተጨማሪ የግብር ከፋዩን ማህበረሰብ ግንዛቤ የማሳደግና ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የህግ ተገዥነትን ለማጠናከር እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

በክልሉ ከ122 ሺህ በላይ የደረጃ "ሀ" እና "ለ" ግብር ከፋዮች መኖራቸውን የጠቀሱት ሃላፊው፣ በክልሉ ኢኮኖሚው የሚያመነጨውን ግብር በአግባቡ በመሰብሰብ ከክልሉ ዓመታዊ በጀት 75 በመቶ የሚሆነውን በውስጥ አቅም ለመሸፈን ታቅዷል ብለዋል።

የገቢ ስርአቱ በዲጂታል ቴክኖሎጂ እንዲታገዝ በመደረጉ ከ63 ሺህ በላይ ግብር ከፋዮች በቴሌ ብር አማካኝነት ግብራቸውን እንደከፈሉ አስታውቀዋል።

በዚህም ግብር ከፋዮች ጊዜና ጉልበታቸውን ሳያባክኑ ባሉበት ቦታ ሆነው ግብር ለመክፈል መቻላቸውን አመልክተዋል።


በክልሉ ከሚገኙ ግብር ከፋዮች መካከል በአርባ ምንጭ ከተማ በጨርቃ ጨርቅ ንግድ ሥራ የተሰማሩት አቶ አለማየሁ ያላ እንዳሉት፤ ግብር መክፈል ለሀገር ዕድገትና ብልፅግና የማይተካ ሚና አለው።

"ግብር መክፈል የዜግነት ግዴታዬ በመሆኑ የሚጠበቅብኝን ግብር በወቅቱ በመክፈል በሀገር ልማትና እድገት ላይ የድርሻዬን እንደተወጣሁ አስባለሁ" ብለዋል።

የግብር አከፋፈል ሥርዓቱ በቴክኖሎጂ የታገዘ በመሆኑ ግብራቸውን ሳይጉላሉ መክፈላቸው ጊዜና ጉልበታቸውን በመቆጠብ ለሌላ ሥራ ለመዋል እንዳስቻላቸው ተናግረዋል።

ገቢ የሚሰበስቡ ተቋማት በየጊዜው በሚወጡ የግብር ህጎችንና መመሪያዎች ላይ የግብር ከፋዩን ማህበረሰብ ግንዛቤ ማሳደግ እንዳለባቸውም ገልጸዋል።


ግብር ለማህበራዊ ልማቶችና ለመሠረተ ልማት ዝርጋታ ትልቅ ፋይዳ አለው ያሉት ደግሞ ሌላኛው ግብር ከፋይ አቶ ታከለ ምትኩ ናቸው።

ግብር መክፈል የዜግነት ግዴታ በመሆኑ ግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ግዴታውን በወቅቱ መወጣት አለበት ብለዋል።

ለሀገር ዕድገት ግብር ወሳኝ በመሆኑ ለዘመኑ የሚጠበቅባቸውን ግብር በመክፈል ሃላፊነታቸውን መወጣታቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ምክር ቤቱ ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል የብድር ስምምነትን አፀደቀ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚው...

Oct 14, 2026

በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅ ላይ ትኩረት ተሰጥቷል

መቱ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):- በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ገቢና የአካባቢውን አምራቾች ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅና...

Sep 23, 2026

በክልሉ ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በማዋል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠና...

Sep 18, 2026

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026