የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶች እውን እንዲሆኑ የድርሻችንን እንወጣለን

Oct 26, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አሶሳ፤ ጥቅምት 14/2019 (ኢዜአ):- የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ለማረጋገጥ የሚደረጉ ጥረቶች እውን እንዲሆኑ የድርሻቸውን እንደሚወጡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች ገለጹ።

ኢዜአ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያነጋገራቸው የተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች እንደገለጹት፣ የባህር በር ጉዳይ ከማንኛውም የፖለቲካ ልዩነት በላይ የሆነ የህልውና ጉዳይ ነው።

የኢኮኖሚ ዕድገት መሠረትና ብሔራዊ አጀንዳ መሆኑንም ያነሱት አመራሮቹ፣ የሀገርን ብሔራዊ ጥቅም ለማስከበርና የሕዝቦችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተጀመረውን ጥረት እንደሚደግፉ ገልጸዋል።

የቤኒሻንጉል ሕዝብ ነፃነት ንቅናቄ (ቤህነን) ሊቀመንበር አቶ አብዱሰላም ሸንገል እንደተናገሩት፤ የባህር በር አጀንዳ የሀገሪቱን ሁለንተናዊ የኢኮኖሚ ዕድገት ያገናዘበ ህጋዊ መሰረት ያለው ነው።

ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባህር በር ጥያቄዋን ለማረጋገጥ የጀመረችው ጥረት በታሪክም ሆነ በዓለም አቀፍ ህግ ተቀባይነት ያለው በመሆኑ ለስኬቱ የሁሉም ዜጋ የጋራ ጥረት ያስፈልጋል ብለዋል።

ፓርቲያቸው በባህር በር ላይ ምንም አይነት የሀሳብ ልዩነት የለውም ያሉት ሊቀመንበሩ፤የተጀመረውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት እንደሚደግፉም አመልክተዋል።

የባሕር በር ባለቤትንት ጥያቄ የሕልውና ጉዳይ መሆኑን ያነሱት አቶ አብዱሰላም፣ ጥያቄው ከዳር እንዲደርስ የበኩላቸውን ሚና ለመወጣት ዝግጁነታቸውን አረጋግጠዋል።

በተመሳሳይ የጉሙዝ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጉህዴን) ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ለሜሳ ኔኖ በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ ባህር በሯን ያጣችው በወቅቱ በነበሩ ታሪካዊ ስህተቶች እንዲሁም በውስጣዊና ውጫዊ ተጽዕኖዎች መሆኑን አስታውሰዋል።

አሁን ላይ በታሪክ የራሷ የነበረውን የባህር በር በሰላማዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ማስመለስ የምትችልበት ወቅት ላይ መሆኗን አንስተዋል።

የመደመር መንግስትና መላው ህዝብ በጉዳዩ ላይ የያዙት ጠንካራ አቋም የሚበረታታ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህ አጋጣሚ ተፎካካሪ ፓርቲዎች በሀገራዊና ብሔራዊ አጀንዳዎች ላይ ያላቸውን የጋራ አቋም በተግባር የሚያሳዩበት መሆኑን ተናግረዋል።

መንግሥት ጉዳዩን በሰጥቶ መቀበል መርህና በቀጠናዊ ትብብር ለማሳካት የያዘው አቋምና እያደረገ ያለው ጥረት ፍትሐዊ መሆኑንና ይህም አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ድጋፍ እያገኘ መምጣቱን ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤትነት መረጋገጥ ለቀጣናው ሀገራት ጭምር አብሮ ማደግና ትሰስር ወሳኝ በመሆኑ የሚደረጉ ጥረቶች እንዲሳኩ ፓርቲው የበኩሉን ይወጣል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ምክር ቤቱ ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል የብድር ስምምነትን አፀደቀ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚው...

Oct 14, 2026

በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅ ላይ ትኩረት ተሰጥቷል

መቱ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):- በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ገቢና የአካባቢውን አምራቾች ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅና...

Sep 23, 2026

በክልሉ ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በማዋል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠና...

Sep 18, 2026

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026