🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 17/2019 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ ለሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ የሰጠችው ትኩረት የሚበረታታ መሆኑን ዓለም አቀፍ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ምሁር እና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ማሞ ሙጬ ገለጹ።
ዘርፉን በጥናትና ምርምር ማገዝ የሚያስችሉ ሥራዎችን ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እየሠሩ መሆኑንም ጠቁመዋል።
የመደመር መንግሥት በትኩረት እየሠራባቸው ካሉ ዘርፎች መካከል የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ተጠቃሽ ሲሆን፣ የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ትኩረት ከተሰጣቸው አምስቱ የኢኮኖሚ አምዶች ውስጥ አንዱ ነው።
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ትግበራም በሳይንስ፣ ዲጂታልና ቴክኖሎጂ ዘርፍ በርካታ ስኬቶች የተመዘገቡ ሲሆን፣ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂም በርካታ ትልሞችን ለማሳካት በመተግበር ላይ ይገኛል።
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት በማቋቋም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ውጤታማ ሥራዎች እየተከናወኑ ሲሆን፣ የመደመር አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዩኒቨርሲቲ ግንባታም የዘርፉ ስኬት ማሳያ ነው።
ስታርትአፖችን ለማበረታታትና የታዳጊዎችን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕውቀትና ክህሎት ለማሳደግ የሚያስችሉ መሠረተ ልማቶችም ተከናውነዋል።
የዓለም አቀፍ የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ምሁር እና ተመራማሪ ፕሮፌሰር ማሞ ሙጬ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የሳይንስ ሙዚየምን መጎብኘታቸውን ገልጸው በሙዚየሙ ያዩት የሚደነቅ ተግባር ነው።
ሙዚየሙ ኢትዮጵያ በቴክኖሎጂ፣ በሳይንስና በኢኖቬሽን ላይ አተኩራ እየሠራች ያለችው ተግባር ማሳያ መሆኑንም ተናግረዋል።
ህፃናትን ጨምሮ ከሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች ታዳጊዎችና ወጣቶች በቴክኖሎጂው ዘርፍ መሳተፋቸው ትውልድን ለነገ የማዘጋጀት ተግባር መሆኑንም ገልጸዋል።
ታዳጊዎችና ወጣቶች በሳይንስ፣ በሰው ሠራሽ አስተውሎትና በዲጂታል ቴክኖሎጂ ያላቸው አቅምና የሚያከናውኑት ተግባርም የሚበረታታ መሆኑን ተናግረዋል።
ተጨማሪ ጥናትና ምርምሮችን በማድረግ ኢትዮጵያን ከዘርፉ የበለጠ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራትን ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን እየሠሩ መሆኑን ጠቁመዋል።
ለተለያዩ ሀገራት በዘርፉ በርካታ እያከናወኑ መሆኑን ጠቅሰው፤ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎችን በተለያዩ መርሃ ግብሮች በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ እንዲደግፉ ለማድረግ እየሠሩ መሆኑንም ገልጸዋል።
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚው...
Oct 14, 2026
መቱ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):- በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ገቢና የአካባቢውን አምራቾች ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅና...
Sep 23, 2026
አሶሳ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በማዋል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠና...
Sep 18, 2026
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026