🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 17/2019 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ መንግሥት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥና ወደ ሙሉ የምግብ ሉዓላዊነት ለመሸጋገር እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት የሚደነቁ መሆናቸውን በኢትዮጵያ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ዳይሬክተር ዝላታን ሚሊሲክ ገለጹ።
በስንዴ ምርት በአፍሪካ ግዙፍ አምራች ሀገር መሆን የቻለችው ኢትዮጵያ፣ በግብርናው ዘርፍ የምግብ ዋስትናን እና ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ያከናወነቻቸው ሥራዎች ተጨባጭ ውጤት አስመዝግበዋል።
በተለይም የበጋ የመስኖ ስንዴ ልማት፣ የሌማት ትሩፋት መርሃ-ግብር እንዲሁም አዳዲስ እርሻዎችን ወደ ምርታማነት የመቀየር አሰራሮችን በመተግበር ከዚህ ቀደም የነበረውን የምግብ አቅርቦት እጥረት በዘላቂነት ማቃለል ተችሏል።
እነዚህ አጠቃላይ የልማት ስልቶች ሀገሪቱ በምግብ ራሷን ከመቻል አልፋ የሌሎችንም ፍላጎት ለማሟላት ለምታደርገው ጥረት ጠንካራ መሠረት ጥለዋል።
በዚህም ምክንያት በዘርፉ የተመዘገቡት አበረታች ስኬቶች ኢትዮጵያ የምግብ ሉዓላዊነቷን በተግባር እያረጋገጠች ለመሆኗ ማረጋገጫ ሆነዋል።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዝላታን ሚሊሲክ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ውጤታማና አስደናቂ ተግባራትን እያከናወነች ትገኛለች።
መንግሥት በቴክኖሎጂ፣ በመሠረተ ልማት፣ በውኃ አስተዳደር እንዲሁም ግብርናን የሚያሳድጉ ቁልፍ ዘርፎች ላይ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት በማድረግ በርካታ ሥራዎችን ማከናወኑን አስታውቀዋል።
ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ ምርጥ ዘሮችን በመጠቀምና ከዚህ ቀደም ለእርሻ አገልግሎት ያልዋሉ መሬቶችን ወደ ምርታማነት በመቀየር በኩል ተጨባጭ ለውጦች መመዝገባቸውንም ጠቁመዋል።
በተጨማሪም የመስኖ ልማት፣ የውኃ አስተዳደር ሥርዓት እና የጎርፍ አደጋዎችን አስቀድሞ ለመቆጣጠር የሚያስችሉ ተግባራት በትኩረት መከናወናቸውን አመልክተዋል።
የግብርና ቴክኖሎጂን መጠቀም በአገር ደረጃ ልዩ ልዩ ምርቶች በከፍተኛ ሁኔታ እንዲመረቱና የግብርና ምርታማነት እንዲያድግ ማስቻሉንም ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ከስምንትና ከአሥር ዓመታት በፊት ከነበረበት ጊዜ ጋር ሲነጻጸር እስከ አሥር እጥፍ የሚደርስ ከፍተኛ የምርት እድገት መታየቱንና የተለያዩ የምርት ዓይነቶች እየተመረቱ እንደሚገኙ አስታውቀዋል።
በአሁኑ ወቅት በአገር ውስጥ የምግብ አቅርቦት እያደገ፣ ወደ አገር ውስጥ የሚገባው ምርት እየቀነሰና ወደ ውጭ የመላክ አቅም እየጎለበተ መምጣቱንም አንስተዋል።
በግብርናው ዘርፍ እየተመዘገበ ያለው ይህ በጎ ውጤት ኢንቨስትመንቱን ይበልጥ በመደገፍ ዘርፉን የበለጠ ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ አመላካች መሆኑን ገልጸዋል።
በተጨማሪም የማህበረሰቦችን የመቋቋም አቅም ማሳደግ፣ የኑሮ ጥበቃን ማጠናከር፣ የፋይናንስ አካታችነትን ማረጋገጥ እና አርሶ አደሮችን ከገበያ ጋር ማገናኘት ላይ ትኩረት አድርገው የሚሰሩ ሥራዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን አብራርተዋል።
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚው...
Oct 14, 2026
መቱ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):- በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ገቢና የአካባቢውን አምራቾች ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅና...
Sep 23, 2026
አሶሳ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በማዋል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠና...
Sep 18, 2026
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026