የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለልማት ተነሺዎች የተገነባውን የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ የተቀናጀ የመኖሪያ መንደር መርቀው ለተጠቃሚዎቹ አስተላለፉ

Nov 2, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 22/2019 (ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለልማት ተነሺ አርሶ አደሮች የተገነባውን የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ የተቀናጀ የመኖሪያ መንደር መርቀው ለተጠቃሚዎች አስተላልፈዋል።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዚሁ ወቅትአዲስ አበባን በጋራ፣ በትብብር እና በውጤታማነት እያለማን እንገኛለን ብለዋል።


ይህም አዲስ አበባን በዓለም አቀፍ መድረክ እንድትሸለም እያስቻላት መሆኑን ተናግረዋል።

እውቅናው የሁሉም ትብብር ውጤት መሆኑን አንስተው፣ የልማት ተነሺዎች ለልማት ተባባሪ መሆናቸው ለዚህ ውጤታማነት አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸዋል።

አዲስ አበባን የማልማቱ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት ከንቲባዋ፣ ዛሬም ለልማት ለተነሱ አርሶ አደሮች ዘመናዊ የሆነ የመኖሪያ ቤት ተገንብቶ መሰጠቱን ተናግረዋል።

ልማት ማለት የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል፣ የኢኮኖሚ አቅሙን ማጠናከርና የነገ ተስፋውን ማለምለም ጭምር ነው ሲሉ ተናግረዋል።

መኖሪያ መንደሩ የነዋሪዎቹን ማኅበራዊ ትስስር በማጠናከር ወደ ተሻለ የአኗኗር ዘይቤ የሚያሸጋግርና ሰው ተኮር የአሠራር አቀራረብን የተከተለ ነው ብለዋል፡፡


ለአርሶ አደሮቹ የኑሮና የገቢ ምንጮቻቸውን የሚያሳድጉበትን ዕድል የሚፈጥሩ በርካታ አቅርቦቶችን ያካተተ መሆኑንም አብራርተዋል።

በመንደሩ የወተት ላሞች ማደሪያ ሼዶችና የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያ፣የንግድ ሱቆች፣ የምርት ማከፋፈያና መሸጫ መጋዘን እንዲሁም ወፍጮዎች፣ የስፖርት ማዘውተሪያ፣ የሕፃናት መጫወቻና ማቆያ ማዕከል እና መሰብሰቢያ አዳራሽ ይገኙበታል ብለዋል።


ከንቲባዋ ለልጆቻችን እና ለመጪው ትውልድ ዘመናዊ እና የሚኮሩባትን ከተማ የመገንባቱ ሥራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው የተናገሩት።

የቦሌ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አደፍርስ ኮራ በበኩላቸው፣ የተገነባው ቤት ነዋሪዎቹ የተሻለ ኑሮ እንዲኖሩ ለማስቻል ታስቦ በዘመናዊ መንገድ መገንባቱን አስታውቀዋል።

የመኖሪያ ቤት የተረከቡ ነዋሪዎች በበኩላቸው፣ኑሯቸውን በአግባቡ ለመምራት የሚያስችሉ መሠረተ ልማቶች እንዲሁም ሌሎች አስፈላጊ አገልግሎቶች በተሟሉበት መንደር በመግባታቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።

ለዚህም ለከተማ አስተዳደሩ ምስጋና አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ምክር ቤቱ ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል የብድር ስምምነትን አፀደቀ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚው...

Oct 14, 2026

በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅ ላይ ትኩረት ተሰጥቷል

መቱ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):- በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ገቢና የአካባቢውን አምራቾች ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅና...

Sep 23, 2026

በክልሉ ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በማዋል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠና...

Sep 18, 2026

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026