የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

በአማራ ክልል ከተሞችን ለኑሮ ምቹና ውብ የማድረግ የተቀናጀ ልማት እየተከናወነ ነው -ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

Nov 2, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ደብረ ብርሃን፤ ጥቅምት 22/2019 (ኢዜአ)፡-የአማራ ክልል ከተሞችን ከማስዋብ ጎን ለጎን ለነዋሪዎችና ለጎብኚዎች ምቹ የማድረግ የተቀናጀ የልማት ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ከለጹ።

የደብረ ብርሃን ከተማን እድገት ለማፋጠን የሚያስችሉ ከ1 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነቡ የተለያዩ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ተመርቀው ለአገልግሎት በቅተዋል።


በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ዛሬ ተመርቀው ለአገልግሎት ከበቁት የልማት ፕሮጀክቶች መካከል መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ የደብረ ብርሀን ከተማ ዘመናዊ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያና ማስወገጃ ፣ የኮሪደር ልማት፣ የከተማ አሥተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ ሕንጻ ግንባታና ሌሎች ፕሮጀክቶች ይገኙበታል።


የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በዚህ ወቅት እንዳሉት በክልሉ ከተሞችን ከማስዋብ ባለፈ ለነዋሪዎችና ለጎብኚዎች የተመቹ ለማድረግ የተቀናጀ የልማት ሥራ እየተከናወነ ነው።

ጽዱ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ እና ጤናው የተጠበቀ ማኅበረሰብ እንዲኖር እንዲህ አይነት የልማት ሥራዎች አስፈላጊ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

ዛሬ በከተማዋ ከተመረቁት ውስጥ በተለይ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያና ማስወገጃ ፕሮጀክት ጽዱ ከተማን ለመፍጠር ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነም አንስተዋል።


መሶብ አንድ ማዕከል አገልግሎትን በማስፋፋትና በዲጂታል የታገዘ አገልግሎት በመስጠት የተገልጋይ እርካታን የማረጋገጥ ሥራም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል።

ደብረብርሃን ከተማ ለኢንዱስትሪና ለኢንቨስትመንት ተመራጭ እንደመሆኗ የተገነቡት መሰረተ ልማቶች ባለሀብቱና ማህበረሰቡ ፈጣንና የተሻለ አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ብለዋል።

መሰረተ ልማቶቹን በአግባቡ መጠቀም ከተማዋን የኢንዱስትሪ እና የአገልግሎት መስጫ ማዕከል ለማድረግ እንደሚያስችላት ገልጸው፣ ለአገልግሎት የበቁትን ፕሮጀክቶች በአግባቡ መጠበቅ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።


የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ በድሉ ውብሸት እንደገለጹት፣ ደብረ ብርሃን ከተማን በኢንዱስትሪ፣ በኢንቨስትመንትና በቱሪዝም ተመራጭ ለማድረግ እየተሰራ ነው።

ዛሬ የተመረቁት መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት፣ ዘመናዊ የፍሳሽ ቆሻሻ ማጣሪያና ማስወገጃ፣ የኮሪደር ልማትና ሌሎች ፕሮጀክቶች ለዚህ ማሳያ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

የልማት ፕሮጀክቶቹ የከተማዋን አድገት ለማፋጠንና ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል ፋይዳቸው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።

ወደሥራ በገባው መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት 12 ተቋማት 65 የተለያዩ አገልግሎቶችን መስጠት መጀመራቸውን ጠቁመው፣ ይህም ብልሹ አሰራርን ለማስቀረት ያስችላል ብለዋል።


በምርቃቱ ላይ የአማራ ክልል ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ይርጋ ሲሳይና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ምክር ቤቱ ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል የብድር ስምምነትን አፀደቀ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚው...

Oct 14, 2026

በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅ ላይ ትኩረት ተሰጥቷል

መቱ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):- በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ገቢና የአካባቢውን አምራቾች ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅና...

Sep 23, 2026

በክልሉ ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በማዋል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠና...

Sep 18, 2026

የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው- ርእሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...

Sep 11, 2026