🔇Unmute
አርባ ምንጭ፣ ጥቅምት 23/2019 (ኢዜአ) ፡-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመሬት አስተዳደር ሥርአትን በማዘመንና ህገወጥ የመሬት ወረራን በመከላከል የሕዝብን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማሳደግ የተጀመሩ ተግባራት እንደሚጠናከሩ ተገለጸ።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመሬት አስተዳደር ቢሮ አንደኛ ሩብ ዓመት አፈጻጸምና የቀጣይ መቶ ቀናት ዕቅድ ላይ ያተኮረ የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ ዛሬ በአርባ ምንጭ ከተማ ተካሂዷል።

በመድረኩ ላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ሃላፊ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ እንዳሉት፤ መሬት ለክልሉ ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ የማይተካ ሚና አለው።
መሬት ውስን ሀብት በመሆኑ በክልሉ ሀብቱን ለይቶ ባለቤትነትን ለማረጋገጥ እንዲሁም በዘርፉ የሚስተዋለው ሙስናና ብልሹ አሰራሮች ለማስወገድ በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱንም ገልጸዋል፡፡
መሬት ለግብርና ምርታማነት፣ ለከተሞች ዕድገት፣ ለኢንዱስትሪና ለቱሪዝም ልማት እንዲሁም ለኢንቨስትመንት መጠናከር ያለውን ሚና በማሳደግ ተስፋ ሰጪ ውጤት መመዝገቡንም ተናግረዋል።
በክልሉ መሬትን በአግባቡ ለመጠቀም በተቋማዊ አደረጃጀት፣ በህግ ማዕቀፍ ዝግጅት፣ በመሬት ልኬት፣ በይዞታ ማረጋገጫ እና በዲጅታል ካዳስተር ሥራዎች ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውንም ኢንጂነር ወንድሙ ገልጸዋል።
በሚቀጥሉት መቶ ቀናት የመሬት ሀብት ቆጠራና ምዝገባ ሥርአትን በማጠናከር፣ የዲጂታል ካዳስተር ስርአትን በማዘመን እንዲሁም የመሬት አገልግሎትን በማሻሻል ህገ-ወጥ የመሬት ወረራን ለመከላከልና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ ትኩረት መሰጠቱንም አስታውቀዋል።

የክልሉ መሬት አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ በበኩላቸው ዘላቂ የመሬት አጠቃቀም ስርአት በመዘርጋት ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማሳደግ በቅንጅት እየተሠራ መሆኑን አንስተዋል።
በተለይ ተቋማዊ የመፈጸም አቅምን በማሳደግና በቴክኖሎጂ የተደገፈ የመሬት ይዞታ ልኬትን በማረጋገጥ የህዝቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተሠሩ ሥራዎች ለውጥ ተመዝግቧል ብለዋል።
በተጨማሪም በክልሉ ባሉ ከተሞች ዘመናዊ የዲጂታል አድራሻ ሥርአትን በመዘርጋት የቱሪዝም ዘርፉ እንዲጎለብትና ዜጎች ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ እየተሠራ ነው ብለዋል።
የክልሉ መሬት 4 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሄክታር ስፋት እንዳለው ገልጸው፣ ከዚህ ውስጥ 3 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሄክታሩ የሚሆነው ለእርሻ ሥራ ተስማሚ መሆኑን ተናግረዋል።
የመሬትን የመልማት አቅም ደረጃ መለየት፣ የመሬት አጠቃቀም ፕላን መተግበር እና ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት የሚውሉ መሬቶችን ከይገባኛል ጥያቄ ነፃ ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ጠቁመዋል።
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚው...
Oct 14, 2026
መቱ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):- በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ገቢና የአካባቢውን አምራቾች ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅና...
Sep 23, 2026
አሶሳ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በማዋል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠና...
Sep 18, 2026
ባሕርዳር፤ ጳግሜ 5/ 2018 (ኢዜአ) ፡-የሀገርን ቀጣይ ተስፋ እና የትውልዱን እጣ ፋንታ የተሻለ ለማድረግ የዛሬው ብርታትና ትጋታችን ወሳኝ ነው ሲሉ የአማራ ...
Sep 11, 2026