የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

የሀገር ውስጥ ምርት ስሌትን ወቅታዊ የማድረግ ሥራ የኢኮኖሚውን ትክክለኛ መጠንና ዕድገት ተዓማኒነት የሚያረጋገጥ ነው

Nov 5, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 25 /2019 (ኢዜአ)፦ የየኢትዮጵያ የተሻሻለው ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ስሌት ወቅታዊ የማድረግ ሥራ የሀገርን ኢኮኖሚ ትክክለኛ መጠንና ዕድገት ተዓማኒነት የሚያረጋገጥ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ገለጹ።

ትልቅ ሀገር፤ ትልቅ ሕዝብ፤ ታላቅ ርዕይ

የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስቴር የተሻሻለውን ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ግምገማ ወቅታዊ የማድረግ ሥራ ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ የተሻሻለው የጠቅላላ ሀገር ውስጥ ምርት መረጃ ቋሚ ዓመት ከ2008 ወደ 2017 ዓ.ም ተቀይሯል።


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት፤ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት የሁሉም ነገር መለኪያ በመሆኑ የጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ስሌት ጊዜውን ካልዋጀ ትክክለኛ ዕቅድና መረጃ ማግኘት ያስቸግራል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የተደረገው የቋሚ ዓመት ለውጥ መሠረታዊ መረጃን መሠረት ያደረገና ብዙ አዳጊ የኢኮኖሚ ዘርፎችን ያካተተ መሆኑን ገልጸዋል።

ይህም ሀገራዊ የፋይናንስ ጥልቀትን ለመለካት ወሳኝ አቅምን በመፍጠር ቁጠባን ወደ ምርታማ ዘርፍ ለማሸጋገር እንደሚያስችል ተናግረዋል።

የኢንዱስትሪ፣ የግብርና፣ የቴክኖሎጂ እና ሌሎችም የኢኮኖሚ ዘርፎችን ትክክለኛ ዋጋና ቦታ አመላካች መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ አቅጣጫ የሚያቀላጥፍ፣ ትንበያና የዕድገት ግምትን ወቅታዊ የሚያደርግ መሆኑንም ተናግረዋል።

ለውጡ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑን ገልጸው፤ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ በተሻለ ሁኔታ ማወቅ ያስችላል ብለዋል።

የኢትዮጵያን የተሟላ ኢኮኖሚ በአግባቡ የለካ፣ በማደግ ላይ ያሉ አዳዲስ የኢኮኖሚ ዘርፎችን ያካተተ መሆኑንም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ተዓማኒነትን ለዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት የሚያስተዋውቅ፣ ተዓማኒና ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሥራ ትልቅ ትርጉም ያለው ነው ብለዋል።


የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስትር ዴኤታ አባስ መሐመድ በበኩላቸው፤ የተሻሻለው ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ስሌት የኢኮኖሚ መጠን፣ መዋቅርና የዘርፎችን ዕድገት በአግባቡ መረዳት የሚያስችል ነው ብለዋል።

የተሻሻለው ስሌት ለማክሮ ኢኮኖሚና ለልማት ዕቅድ ዝግጅት፣ ለኢኮኖሚ ፖሊሲ አወጣጥ፣ ለኢንቨስትመንት መስፋፋትና ለልማት ክትትል የሚያግዝ የተሻለ የመረጃ መሰረት ይፈጥራል ብለዋል።


በዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይ ኪዩንግሱክ ሊ በበኩላቸው፤ የጠቅላላ ሀገራዊ ምርት ስሌትን ማሻሻል የኢኮኖሚውን እውነተኛ ሁኔታ በተሻለ ለመረዳትና የስታቲስቲክስ ጥራትን ለማሳደግ ወሳኝ እርምጃ መሆኑን ገልጸዋል።

ኢኮኖሚ እያደገና እየተለወጠ ሲሄድ አዳዲስ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴዎችን፣ የምርትና የፍጆታ ለውጦችን እና የተሻሻሉ መረጃዎችን ለማካተት የኢኮኖሚ ስሌቱ ጊዜውን ጠብቆ መዘመን አለበት ብለዋል።


በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተባባሪ ፕሮፌሰር ታደለ ፈረደ (ዶ/ር)፤ በአዲስ መረጃ፣ በተሻሻለ የአሰራር ዘዴና በአዲስ መነሻ ዓመት የተዘጋጀው ስሌቱ መዋቅራዊ የኢኮኖሚ ስብጥርን በተሻለ ጥራት መረዳት ያስችላል ብለዋል።

የኢኮኖሚ ዘርፎች ለመዋቅራዊ ሽግግር ያላቸውን ሚና በተሻለ መረጃ ለመለካት እንደሚያስችል ገልጸው፤ ለዩኒቨርሲቲዎች የምርምርና የማስተማር ሥራዎች ጠቃሚ መረጃ ይሆናል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማሳደግ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው

ዲላ፣ ጥቅምት 25/2019 (ኢዜአ)፡-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማሳደግ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችሉ ተግባራት እ...

Nov 5, 2026

ምክር ቤቱ ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል የብድር ስምምነትን አፀደቀ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚው...

Oct 14, 2026

በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅ ላይ ትኩረት ተሰጥቷል

መቱ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):- በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ገቢና የአካባቢውን አምራቾች ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅና...

Sep 23, 2026

በክልሉ ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በመጠቀም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር አሻደሊ ሀሰን

አሶሳ፤ መስከረም 7/2019 (ኢዜአ)፦ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ያለውን የውሃ ሀብት ለመስኖ ልማት በማዋል ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት ተጠና...

Sep 18, 2026