የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በማዕድን ዘርፉ እመርታዊ ውጤት አስገኝቷል 

Nov 10, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 30/2019 (ኢዜአ)፡-ኢትዮጵያ ያከናወነችው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በማዕድን ዘርፉ ላይ ትልቅ እመርታዊ ውጤት እንዲመጣ አስችሏል፡፡

የማዕድን ዘርፍ ከአምስቱ የሀገሪቱ ዋና ዋና የኢኮኖሚ ምሰሶዎች አንዱ ሲሆን፣ የዘርፉ ዕድገት ከጊዜ ወደ ጊዜ በፍጥነት እየጨመረ ይገኛል፡፡

የመደመር መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው የላቀ ትኩረትና ባከናወናቸው የማስተዋወቅ ሥራዎች፣ የማዕድን ልማት በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ የኢኮኖሚ ጀርባ አጥንት ወደ መሆን ተሸጋግሯል።

ባለፉት ሦስት አሥርት ዓመታት ውስጥ የማዕድን ዘርፍ ለአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት ያበረከተው አስተዋጽኦ እጅግ አነስተኛ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ግን አስገራሚ መዋቅራዊ ሽግግር እየተመዘገበ ይገኛል።

ኢትዮጵያ ከማዕድን ዘርፍ የምታገኘውን ገቢ ይበልጥ ለማሳደግና እሴት ጨምሮ ወደ ውጭ በመላክ እምርታዊ ለውጥ ለማምጣት በቅርቡ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቦሌ ለሚ ልዩ የኢኮኖሚ ቀጣና የተገነባው ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ ተመርቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በወቅቱ እንደገለጹት፤ የተገነባው ማጣሪያ ፋብሪካ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን ሰፊውን የምሥራቅ አፍሪካና አጠቃላይ የአፍሪካ ገበያን የማገልገል አቅም አለው።

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የወርቅ ማጣሪያ ፋብሪካ ከአፍሪካ ግዙፍ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ተቋማት አንዱ የመሆን እና ወርቅ ማጣራትና ተጨማሪ እሴት ለመፍጠር ቀጣናዊ ማዕከል የመሆን ዓላማን ሰንቋል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ከፍተኛ ፕሮግራም ኦፊሰር ጌታቸው ተክለማርያም እንደገለጹት፣ ኢትዮጵያ በበርካታ የማዕድናት ሀብት የበለጸገች ሀገር ነች።

በዘርፉ ከተደረገው የፖሊሲና የአሠራር ማሻሻያ በኋላ ለዘርፉ በተሰጠው ከፍተኛ ትኩረት ውጤት ማግኘት ተችሏል ብለዋል።

የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የማዕድን ሀብቶችን በአግባቡ በመጠቀም፣ ገቢ ምርትን ለመተካትና የኢንዱስትሪ ዘርፉን ለመደገፍ የሚያስችሉ ዕድሎችን መፍጠሩን ተናግረዋል፡፡

ከዘርፉ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ በጠንካራ የፖሊሲ ማሻሻያዎችና እሴት መጨመር ስራዎች ታግዞ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ ከፍተኛ ዕድገት ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡


የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ተመራማሪ ጋሻው አይፈራም (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ መንግሥት ለዘርፉ በሰጠው ቀዳሚ ትኩረት ምክንያት ታይቶ የማይታወቅ የገቢና የኤክስፖርት መጠን እየተመዘገበ ይገኛል።

የፖሊሲ ማዕቀፉ ጥሬ ዕቃዎችን በቀጥታ ከመላክ ይልቅ እሴት በመጨመር ላይ ያተኮረ መሆኑን አንስተዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ብሔራዊ የውድ ማዕድናት ማጣሪያ ፋብሪካ መመረቁን ጠቁመው የተፈጥሮ ጋዝ ማጣሪያ ፋብሪካዎችን ጨምሮ ሌሎችንም የመገንባት ሥራዎች ቅድሚያ ተሰጥቶ እየተሰራ መሆኑን አድንቀዋል፡፡

እየተከናወኑ የሚገኙ ውጤታማ ተግባራት እና የፖሊሲ አቅጣጫዎች ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ የማዕድናት ማዕከል እንድትሆን የሚከናወኑ እንቅስቃሴዎች አካል በመሆናቸው ለቀጣይ የአገሪቱ የኢኮኖሚ ጉዞ ከፍተኛ ጥቅም የሚሰጡ መሆናቸው ተመላክቷል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

በክልሉ ቀድመው የደረሱ ሰብሎችን በተፋጠነ ሁኔታ የመሰብሰብ ስራ እየተከናወነ  ነው

ጎንደር ፣ ጥቅምት 29/2019 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ቀድመው የደረሱ ሰብሎችን በቴክኖሎጂ ታግዞ የመሰብሰብ ሥራ በተፋጠነ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ በም...

Nov 9, 2026

በክልሉ የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማሳደግ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው

ዲላ፣ ጥቅምት 25/2019 (ኢዜአ)፡-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማሳደግ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችሉ ተግባራት እ...

Nov 5, 2026

ምክር ቤቱ ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል የብድር ስምምነትን አፀደቀ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚው...

Oct 14, 2026

በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ተጠቃሚነት ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅ ላይ ትኩረት ተሰጥቷል

መቱ፤ መስከረም 12/2019 (ኢዜአ):- በኢሉባቦር ዞን ከቡና ምርት የሚገኘውን ገቢና የአካባቢውን አምራቾች ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ በቡና ጥራት አጠባበቅና...

Sep 23, 2026