🔇Unmute
ዲላ፤ ህዳር 5/2019 (ኢዜአ)፦ በአፍሪካ የታዳሽ ኃይል ልማት ኢትዮጵያ የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች መሆኑን በኖርዌይ የላይፍ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ተመራማሪ ፕሮፌሰር ሳሙኤል አዳራሞላ ገለጹ።
ፕሮፌሰሩ በጉዳዩ ላይ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት፤ ኢትዮጵያ ለኃይል ማመንጫ የሚሆን ትልቅ የውኃ ሀብት ያላት ሀገር ናት።
ኢትዮጵያ ያላትን የውኃ ሀብት አልምታ ለኃይል ምንጭነት በመጠቀም ረገድ ከአፍሪካ ቀዳሚ እንደሚያደርጋት ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ከንፋስ ኃይል የማመንጨት አቅም ያላት መሆኑን ጠቁመዋል።

በአዳማ፣ አሸጎዳና ሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች የሚገኙትን የንፋስ ኃይል ማመንጫዎችን ለአብነት ጠቅሰዋል።
እንዲሁም ከእንፋሎትና ከባዮማስ ኃይል የማመንጨት ትልቅ አቅም ያላት መሆኑን ጠቁመው፤ በታዳሽ ኃይል ልማት በአፍሪካ የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ስለመሆኑ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ በአጠቃላይ ትልቅ የሆነ የታዳሽ ኃይል አቅም ያላት መሆኑን ጠቁመው፤ ለዘርፉ ልማት ትኩረት በመስጠት የውኃ፣ የንፋስና የእንፋሎት ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶችን በመገንባት አገልግሎት እንዲሰጡ እያደረገች ትገኛለች ብለዋል።
በዚህ የልማት እንቅስቃሴም የኢትዮጵያ ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸዋል።
የታዳሽ ኃይል ሀብቶችን በቅንጅትና በትብብር ማልማት ከተቻለ ከምሥራቅ አፍሪካ ቀጠና አልፎ የአፍሪካን የነዳጅ ጥገኝነት ጫና የሚያቃልል መሆኑን አመልክተዋል።

በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ውኃን ጨምሮ የታዳሽ ኃይልን በጋራ የመጠቀም አቋሟ የሚበረታታ መሆኑን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በአረንጓዴ ኢኮኖሚ ዘርፍ እያራመደችው ያለው የልማት አቅጣጫ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልና በግብርና ዘርፍ ለምርት ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህም ከራሷ አልፎ ለሌሎች የአፍሪካና የዓለም ሀገራት በምሳሌነት የምትጠቀስ ያደርጋታል ሲሉ አመልክተዋል።
ዲላ፤ ህዳር 5/2019 (ኢዜአ)፦ በአፍሪካ የታዳሽ ኃይል ልማት ኢትዮጵያ የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች መሆኑን በኖርዌይ የላይፍ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ተመራ...
Nov 16, 2026
ጎንደር ፣ ጥቅምት 29/2019 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ቀድመው የደረሱ ሰብሎችን በቴክኖሎጂ ታግዞ የመሰብሰብ ሥራ በተፋጠነ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ በም...
Nov 9, 2026
ዲላ፣ ጥቅምት 25/2019 (ኢዜአ)፡-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማሳደግ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችሉ ተግባራት እ...
Nov 5, 2026
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚው...
Oct 14, 2026