🔇Unmute
ወልቂጤ ፤ ህዳር 5/2019 (ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሰብአዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን የለማው የበቆሎና የጤፍ ምርት መሰብሰብ መቻሉን የልዩ ወረዳው አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
የቀቤና ልዩ ወረዳ አደጋና ሥጋት መከላከል ሥራ አመራር ዘርፍ ኃላፊ አቶ አዩብ ታጁ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ሰብአዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን እና ከተረጂነት ለመውጣት የምግብ ሰብል ክምችትን የማሳደግ ሥራ እየተሠራ ይገኛል።

በልዩ ወረዳው ያለውን ምቹ ሁኔታ በመጠቀም በግብርናው ዘርፍ የተለያዩ የሰብል ዓይነቶችን በማልማት ሰብአዊ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ዜጎች የማዳረስ ሥራ እየተሠራ ነው ብለዋል።
ለዚህም በተለያዩ አካባቢዎች ለሰብአዊ ድጋፍ እንዲውል የተዘራውን ሰብል በማሰባሰብ ወደ መጋዘን የማስገባት ሥራ እየተከናወነ እንደሆነም አንስተዋል።
በዘንድሮው ዓመትም በ30 ሄክታር መሬት ላይ በቆሎና ጤፍ መለማቱን ገልጸው፤ 800 ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉንም ጠቁመዋል።
ይህም በልዩ ወረዳው ሰብአዊ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች በራስ አቅም ድጋፍ ማድረግ የሚያስችል መሆኑን ጠቅሰዋል።
ቀጣይነት ያለው ሰብአዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሻገር በልዩ ወረዳው ሁሉንም ማኅበረሰብ አደረጃጀቶች በመጠቀም የተሻለ ሥራ እንደሚሠራም አመልክተዋል።
ዲላ፤ ህዳር 5/2019 (ኢዜአ)፦ በአፍሪካ የታዳሽ ኃይል ልማት ኢትዮጵያ የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች መሆኑን በኖርዌይ የላይፍ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ተመራ...
Nov 16, 2026
ጎንደር ፣ ጥቅምት 29/2019 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ቀድመው የደረሱ ሰብሎችን በቴክኖሎጂ ታግዞ የመሰብሰብ ሥራ በተፋጠነ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ በም...
Nov 9, 2026
ዲላ፣ ጥቅምት 25/2019 (ኢዜአ)፡-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማሳደግ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችሉ ተግባራት እ...
Nov 5, 2026
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚው...
Oct 14, 2026