የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
ልዩ ዘገባ

በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን የሚገኙ ነዋሪዎች ቡና ጥራትና ደረጃን ለማስጠበቅ የሰጡት ትኩረት ምን ይመስላል?

Nov 19, 2026

IDOPRESS

🔇Unmute

ጅማ ህዳር 09/2019(ኢዜአ) በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን የሚገኙ ነዋሪዎች ለገበያ የሚቀርበውን ቡና ጥራትና ደረጃ ለማስጠበቅ ልዩ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

ቡናን ጥራት አስጠብቆ ለገበያ ለማቅረብ ከአርሶ አደሩ እስከ ማቀነባበሪያ ተቋማት ያሉ ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ጥረት ወሳኝ መሆኑ ይታወቃል።

በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን የሚገኙ ነዋሪዎች ለገበያ የሚቀርበውን ቡና ጥራትና ደረጃ ለማስጠበቅ ልዩ ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በጎማ ወረዳ ቆታ ጩዋ ቀበሌ በሚገኘው የበዴይ ቡና ማቀነባበሪያ ፋብሪካ የሚሠሩት አቶ ኤፍሬም ታምራትና ወይዘሮ ወዚራ ነዚፍ፣ የቡናን ጥራት ማስጠበቅ በዘርፉ የተሰማሩ ሁሉም አካላት ኃላፊነት መሆኑን ገልጸዋል።

ሠራተኞቹ በተቋሙ ሥራ ከመጀመራቸው በፊት ተገቢውን ሙያዊ ሥልጠና ማግኘታቸውን ገልጸው፣ የቡናን ጥራት ማስጠበቅ ከግልና ከተቋም ጥቅም ባለፈ ሀገራዊ ፋይዳ ያለው በመሆኑ ሥራቸውን በከፍተኛ ጥንቃቄ እያከናወኑ መሆናቸውን አስረድተዋል።

ፋብሪካው ቀይ ቡናን በመፈልፈል፣ በማጠብና በማድረቅ ደረጃውን ጠብቆ ለገበያ የማቅረብ ሥራ እያከናወነ ሲሆን፣ የፋብሪካው ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱሰላም አወል ተቋሙ የቡናን ጥራት ለማስጠበቅ በስፋት እየሠራ መሆኑን ገልጸዋል።

በዘንድሮ ዓመትም ካለፈው ዓመት በተሻለ ጥራቱን የጠበቀ ቡና ለገበያ ለማቅረብ ትኩረት tሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል።

የቡና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግም ፋብሪካው የችግኝ ማፍያ ጣቢያ በማዘጋጀት ከፍተኛ ምርት የሚሰጡ የቡና ችግኞችን ለአካባቢውና ለአጎራባች ቀበሌዎች አርሶ አደሮች እያቀረበ መሆኑንም አቶ አብዱሰላም አስረድተዋል።

ፋብሪካው ከቡና ማቀነባበር ሥራው በተጨማሪ ለአካባቢው ማኅበረሰብ የሥራ ዕድል እየፈጠረ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት ከ350 በላይ ሠራተኞች በቡና ማጠብና ማጽዳት ሥራዎች ተሰማርተው እየሠሩ መሆኑን ገልጸዋል።

የደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት የቡና፣ ሻይ፣ ቅመማ ቅመም፣ አትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ ምክትል ኃላፊ አቶ ሚፍታህ ጋሊ፣ በዞኑ የቡናን ጥራት በመጠበቅ የማምረትና የመሰብሰብ ሥራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል ብለዋል።

በዘርፉ ቀጣይነት ያለው ክትትል እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰው፣ በዞኑ የሚገኙ 620 የቡና ማቀነባበሪያ ፋብሪካዎች ቡናን በጥራት አቀነባብረው ለገበያ የማቅረብ ሥራ እያከናወኑ መሆኑን አብራርተዋል።

በደቡብ ምዕራብ ኦሮሚያ ዞን ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር በላይ መሬት በቡና የተሸፈነ ሲሆን፣ በዘንድሮ ዓመት 195 ሺህ 118 ቶን በላይ ጥራቱን የጠበቀ ቡና ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እየተሠራ መሆኑን አቶ ሚፍታህ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ልማት የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች ነው

ዲላ፤ ህዳር 5/2019 (ኢዜአ)፦ በአፍሪካ የታዳሽ ኃይል ልማት ኢትዮጵያ የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች መሆኑን በኖርዌይ የላይፍ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ተመራ...

Nov 16, 2026

በክልሉ ቀድመው የደረሱ ሰብሎችን በተፋጠነ ሁኔታ የመሰብሰብ ስራ እየተከናወነ  ነው

ጎንደር ፣ ጥቅምት 29/2019 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ቀድመው የደረሱ ሰብሎችን በቴክኖሎጂ ታግዞ የመሰብሰብ ሥራ በተፋጠነ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ በም...

Nov 9, 2026

በክልሉ የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማሳደግ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችሉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው

ዲላ፣ ጥቅምት 25/2019 (ኢዜአ)፡-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማሳደግ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችሉ ተግባራት እ...

Nov 5, 2026

ምክር ቤቱ ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚውል የብድር ስምምነትን አፀደቀ

አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚው...

Oct 14, 2026