🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ህዳር 14/2019 (ኢዜአ)፦ አፍሪካ የጤና ደህንነትና ሉዓላዊነቷን በራሷ አቅምና አመራር ማረጋገጥ እንዳለባት የአፍሪካ በሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዣን ካሴያ አስታወቁ።
5ኛው ዓለም አቀፍ የአፍሪካ የሕዝብ ጤና ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
"የአፍሪካ የጤና ደህንነት እና ሉዓላዊነት፤ ከጤና ጥገኝነትና ተጋላጭነት ወደ ባለቤትነትና ጽናት የሚደረግ ሽግግር" በሚል መሪ ሓሳብ በሚካሄደው ጉባኤ ላይ የሀገራት መሪዎች፣ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችና የሕዝብ ጤና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።
በጉባኤው ላይ ንግግር ያደረጉት ዶክተር ዣን ካሴያ፤ ከ135 አገራት የተውጣጡ 46 ሺህ 217 ተሳታፊዎች የተመዘገቡበት ይህ መድረክ በዓለም ትልቁ የሕዝብ ጤና ጉባኤ መሆኑንና ለአፍሪካ ደህንነትና ሉዓላዊነት የሚካሄድ እንቅስቃሴ እንደሆነ ገልጸዋል።
ማዕከሉ የስትራቴጂክ ዕቅዱን 96 በመቶ ማሳካቱን የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሩ፤ በዚህም በአመራር ላይ ያሉ ሴቶች ድርሻ ከ11 በመቶ ወደ 38 በመቶ፣ የክትባት ሽፋን ደግሞ ከ34 በመቶ ወደ 99 በመቶ ማደጉን አብራርተዋል።
ብሔራዊ የሕዝብ ጤና ኢንስቲትዩት ያላቸው አገራት ከ7 ወደ 42፣ የዘረ-መል ልየታ የሚያከናውኑት ደግሞ ከ7 ወደ 52 ከፍ ማለታቸውን ጠቁመው፤ "አፍሪካ ስኬት ናት" ብለዋል።
ማዕከሉ በወረርሽኝ ወቅት ፈጣን ምላሽ እንደሚሰጥ ገልጸው፤ በዩጋንዳ የማርበርግ ወረርሽኝን በሦስት ወራት ውስጥ ለመቆጣጠር መቻሉን፣ በናይጄሪያም የኢቦላ ወረርሽኝ ሪፖርት ከተደረገ ከሁለት ሰዓት በኋላ ድጋፍ ለመስጠት መነሳቱንና በኬንያ ላይ የጉዞ ገደብ እንዳይጣል መከላከሉን አንስተዋል።
ኢትዮጵያ በዲጂታል ጤና እና በሠው-ሰራሽ አስተውሎት ዘርፍ አመርቂ ሥራዎችን ማከናወን መቻሏን ጠቁመዋል፡፡
ለአፍሪካ ጤና ተቋማት የሚለቀቁ የፋይናንስ ድጋፎች ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው መንገድ መመራት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡
የአፍሪካ የጤና ደህንነትና ሉዓላዊነት ራዕይ የራስን ምርት በማምረት፣ ዘርፉን በራስ ገንዘብ በመደገፍ፣ ወረርሽኞችን በራስ አቅም በመምራትና ዲጂታል ሽግግርን በማምጣት ላይ እንደሚያተኩር ገልጸዋል።
ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዕጩዎች በዚህ ጉባኤ ተገኝተው ለአፍሪካ ያላቸውን ዕቅድ እንደሚያቀርቡም አስታውቀዋል።
ወጣቶችም አህጉሪቱና የወደፊቱ ዕድል የእነርሱ መሆኑን ተገንዝበው በራሳቸው ዝግጁ እንዲያደርጉ አሳስበዋል።
በኢትዮጵያ እየታየ ያለውን ፈጣን ለውጥና የአፍሪካ ሲዲሲ ዋና መሥሪያ ቤት ሕንጻን በማድነቅ፣ ለሕንጻው መንገድ እንዲሰራ በጠየቁ ጊዜ ፈጣን ምላሽ ለሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ምስጋና አቅርበዋል።
የአዲስ አበባ ለውጥና እድገት ኢትዮጵያ ለአህጉሪቱ ኩራት እንደሆነች የሚያሳይ ተጨበጭ ተምሳሌት መሆኑንም ገልጸዋል።
ዲላ፤ ህዳር 5/2019 (ኢዜአ)፦ በአፍሪካ የታዳሽ ኃይል ልማት ኢትዮጵያ የመሪነት ሚናዋን እየተወጣች መሆኑን በኖርዌይ የላይፍ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ የዘርፉ ተመራ...
Nov 16, 2026
ጎንደር ፣ ጥቅምት 29/2019 (ኢዜአ)፡- በአማራ ክልል ቀድመው የደረሱ ሰብሎችን በቴክኖሎጂ ታግዞ የመሰብሰብ ሥራ በተፋጠነ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ በም...
Nov 9, 2026
ዲላ፣ ጥቅምት 25/2019 (ኢዜአ)፡-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የገጠር መንገድ ተደራሽነትን በማሳደግ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችሉ ተግባራት እ...
Nov 5, 2026
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 3/2019 (ኢዜአ)፦ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለኃይል ሴክተር ሪፎርም ኢንቨስትመንትና ማዘመኛ ምዕራፍ አንድ ፕሮጀክት ማስፈፀሚያ የሚው...
Oct 14, 2026