
አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮ-ቴሌኮም የኤሌክትሪክ መኪኖችን ባትሪ በፍጥነት መሙላት የሚያስችሉ ሶስት የተለያዩ ቴክኖሎጂዎችን ይፋ አድርጓል።
ቴክኖሎጂዎቹ ተግባራዊ የሚደረጉበት የራሱ የሀይል ማስተላለፊያ ጣቢያ የተዘጋጀለት ሲሆን ይህም በአዲስ አበባ ከመገናኛ ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ኢምፔራያል አካባቢ የሚገኝ ነው።
የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ቴክኖሎጂዎቹ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን የጠበቁና በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚተገበሩ ናቸው ብለዋል።

ከቴክኖሎጂዎቹ መካከል አልትራ ፋስት የተሰኘው የኤሌክትሪክ መኪና ባትሪ መሙያ አንድ ኪሎ ሜትር መጓዝ የሚያስችል ሀይልን በአንድ ሰከንድ የሚሞላ መሆኑን ተናግረዋል።
በተጨማሪም ሱፐር ፋስት የተሰኘው የኤሌክትሪክ ባትሪ መሙያ ቴክኖሎጂ ከ10 እስከ 30 ደቂቃ ድረስ ሙሉ ሀይል መሙላት የሚያስችል ነው ብለዋል።
ሌላኛው የሀይል ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂ ደግሞ ድንገተኛ የሀይል መቋረጥ ሲያጋጥም በሀይል ማስተላለፊያ ጣቢያ ውስጥ ባሉ ፖሎች ላይ በተገጠሙ ቴክኖሎጂዎች አማካኝነት በቀላሉ ሀይል መስጠት የሚያስችል ስለመሆኑም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ገልጸዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026