የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

<p>ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ ፕሮጀክቶች ላይ የተሻለ አፈፃፀም አሳይታለች - ሚኒስትር አህመድ ሽዴ</p>

Feb 12, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ የካቲት 4/2017(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ ፕሮጀክቶች ላይ የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገቧን የኢኒሼቲቩ ፕሮጀክቶች ሰብሳቢና የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ገለፁ።

የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ ቀጣናዊ ፕሮጀክቶች አፈጻጸምን የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በጋራ ገምግመዋል።

የኢኒሼቲቩ ሰብሳቢና የገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ጉዳዩን አስመልክቶ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም ኢኒሼቲቩ በቀጣናው ሀገራት የመሰረተ ልማትና የሰው ሀብት ልማት፣ የግብርና፣ የጤና፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ፣ ዲጂታል ቴክኖሎጂ እንዲሁም አደጋዎች መከላከል ላይ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

እነዚህ የቀጣናው የልማት ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜና በጀት እንዲጠናቀቁ ክትትል የሚደረግ መሆኑንም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የቀጣናው የሰላምና የልማት ማዕከል በመሆኗ ኢኒሼቲቩ ውጤታማ እንዲሆን የማስተባበር ስራውን በትኩረት እየሰራች ትገኛለች ብለዋል።

ከሀገራዊ ለውጡ በኋላ የአፍሪካ ቀንድ ሀገራትን በልማት ለማስተሳሰር የየሀገራቱ የገንዘብ ሚኒስትሮች ያቋቋሙት መሆኑንም አንስተዋል።

ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር በጋራ ለመልማት ካላት ፍላጎት አኳያ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችን እየተገበረች መሆኑን ጠቅሰው፤ እስካሁን ከሶስት ቢሊዮን ዶላር በላይ የልማት ድጋፍ ማግኘቷን አመልክተዋል።

በተለይም በመንገድ፣ በባቡርና በሀይል መሰረተ ልማት ከጎረቤት ሀገራት ጋር ለመተሳሰር የምታደርገው ጥረት ድጋፍ እንድታገኝ አስችሏል ብለዋል።

በመጪው የካቲት 11 ቀን 2017 ዓ.ም የአፍሪካ ቀንድ የገንዘብ ሚኒስትሮችና አጋር አካላት በተገኙበት የኢኒሼቲቩ የፕሮጀክቶች አፈፃፀምና የአምስተኛ ዓመት ምስረታ መድረክ የሚካሄድ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የአፍሪካ ቀንድ ኢኒሼቲቭ በዓለም ባንክ፣ በአውሮፓ ህብረትና፣ በአፍሪካ ልማት ባንክ የገንዘብ ድጋፍ የተመሰረተ ቀጣናዊ የትብብር ማዕቀፍ ሲሆን ኢትዮጵያ ኢኒሼቲቩን ታስተባብራለች።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026

ኢትዮጵያ እና ሩሲያ በሰው ሃይል ልማትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ በጋራ ይሰራሉ - በኢትዮጵያ የሩሲያ አምባሳደር ኤቭጌኒ ቴርኪን

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...

Aug 21, 2026