
ሐረር፤ ሚያዝያ 11/2017(ኢዜአ)፦ በሐረሪ ክልል ለካፒታል ፕሮጀክቶች ልዩ ትኩረት በመስጠት እየተሰራ እንደሚገኝ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ።
ርዕሰ-መስተዳድሩ በክልሉ በግንባታ ላይ የሚገኙ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን እየጎበኙ ነው።
በጉብኝቱ ወቅት ርዕሰ መስተዳድሩ እንደገለጹት በክልሉ የካፒታል ፕሮጀክቶችን በልዩ ትኩረት የመፈጸም እንቅስቃሴ በቅንጅት እየተከናወነ ነው።
ፕሮጀክቶቹ የህዝቡን ጥያቄ መሰረት በማድረግ የሚከናወኑ መሆኑን ጠቁመው ከፍጻሜ ለማድረስም በጥራት፣ በፍጥነትና በኃላፊነት እንዲሰራም አስገንዝበዋል።

በዛሬው ዕለትም ከካቢኔያቸውና ከክልሉ ከፍተኛ አመራር አባላት ጋር በመሆን የሚጎበኟቸው በክልሉ ከተማና ገጠር ወረዳዎች በበጀት ዓመቱ 9 ወራት እየተገነቡ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ነው።
በጉብኝቱም ትምህርት ቤቶች፣ የመንገድ ግንባታ፣ በከተማና ገጠር የሚከናወኑ የኮሪደር ልማት ስራዎች ምልከታ ይካሄድባቸዋል።
እንዲሁም የገበያ ሼድ ግንባታ፣ በግል የሚከናወኑ የኢንቨስትመንት ግንባታዎች፣ የአባድር ፕላዛ የኮሪደር ልማት ግንባታና ሌሎችም እንደሚገኙባቸው ተጠቅሷል።
በተጨማሪም በ3ኛው ዙር የጀጎል ኮሪደር ልማት መርሃ-ግብር እየተከናወኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶች ጉብኝት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።
በጉብኝቱም የክልሉ ካቢኔ አባላትና የሴክተር መስሪያ ቤት ኃላፊዎች ተገኝተዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026