
አዲስ አበባ፤ ሚያዝያ 14/2017(ኢዜአ)፦የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ተጠሪ ተቋማት እና የብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት የሥራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የተለያዩ የልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው።
ጉብኝቱ በከተማዋ የተከናወኑ እና በመከናወን ላይ የሚገኙ የኮሪደር ልማት ስራዎችን፣ የመልሶ ማልማትና የወንዝ ዳርቻ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ ሌሎች በርካታ የልማት ሥራዎችን ያካተተ መሆኑ ተጠቁሟል።
በአዲስ አበባ እየተከናወኑ የሚገኙ የልማት ሥራዎች ለነዋሪዎች ምቹ አካባቢ የሚፈጥሩና የከተማዋን ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነት በእጅጉ የሚያሳድጉ መሆናቸውም ተገልጿል።
በተጨማሪም የልማት ሥራዎቹ አዲስ አበባን የተቀናጀ የመሠረተ ልማት የተሟላላት ከተማ እንድትሆን የሚያስችሉ ናቸው ተብሏል።
በከተማዋ ባለፉት ጥቂት ዓመታት የዓድዋ ድል መታሰቢያ፣ የአዲስ ዓለም ዓቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል፣ የነገዋ የሴቶች ተሐድሶ ማዕከል፣ የተለያዩ ሰው ተኮር ፕሮጀክቶች እንዲሁም ሌሎች በርካታ የልማት ስራዎች መከናወናቸው ይታወቃል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026