የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የሴቶችና ወጣቶችን አቅም የበለጠ በመጠቀም የአፍሪካን ትራንስፎርሜሽን ማፋጠን ይገባል - አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ

May 8, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 29/2017 (ኢዜአ)፦የሴቶችና ወጣቶችን አቅም የበለጠ በመጠቀም የአፍሪካን ትራንስፎርሜሽን ማፋጠን እንደሚገባ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ገለፁ።

ዛሬን ጨምሮ ለሶሰት ቀናት የሚቆየው ስድስተኛው የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) ሴት ሥራ ፈጣሪዎች የንግድ ትርዒትና ኮንፈረንስ በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በንግድ ትርዒቱ መክፈቻ ላይ እንዳሉት፣ አፍሪካ በ2063 ለማሳካት ከያዘቻቸው አጀንዳዎች አንዱ የሴቶችን እኩልነትና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው።

ለአፍሪካ ዘላቂና አስተማማኝ ዕድገት የተቀናጀና የተናበበ ስራ ወሳኝ ሚና እንዳለውም አንስተዋል።

ኢትዮጵያ የኮሜሳ መስራች መሆኗን አስታውሰው፤ ለአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነትን ውጤታማ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እያደረገች መሆኑንም አመልክተዋል።

የሴቶችና ወጣቶችን አቅም የበለጠ በመጠቀም የአፍሪካን ትራንስፎርሜሽን ማፋጠን እንደሚገባም ነው ያመለከቱት።

ኢትዮጵያ ያደረገችው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለግሉ ዘርፍ ምቹ ሁኔታ የፈጠረና ተወዳዳሪነትን ያሳደገ ነው ብለዋል።

ኮሜሳ ለሴት ስራ ፈጣሪዎች እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) በበኩላቸው እንደገለጹት፤ የኮሜሳ አባል አገራት ሴቶች በንግድ እንቅስቃሴ ውስጥ ጉልህ ሚና አላቸው።

የሚያጋጥማቸውን ፈተናዎች ተቋቁመው በንግድ ሥራ ውጤታማ የሆኑ ሴቶች መኖራቸውንም አንስተዋል።

ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ውህደት በቁርጠኝነት እየሰራች መሆኑን አመልክተው፤ በዘርፉ የሚያግጥሙ ተግዳሮቶችን ለይታ ለመፍትሄው እየሰራች ነው ብለዋል።

የበለፀገች አፍሪካን እውን ለማድረግ የኮሜሳ አባል አገራት የበለጠ ተቀናጅተው ሊሰሩ እንደሚገባም አመልክተዋል።

በንግድ ትርዒትና ባዛሩ ላይ ከ200 በላይ የኮሜሳ አባል አገራት ሴት ስራ ፈጣሪዎች ምርትና አገልግሎታቸውን አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026