
ባህርዳር፤ ግንቦት 3/2017(ኢዜአ)፦ የባህር ዳር የኮሪደር ልማት ለከተማዋ መስህብነት ተደማሪ ኃብት እና ጸጋ ሆኗል ሲሉ የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ገለጹ።
የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች የኮሪደር ልማቱ አካል የሆነው የስማርት ፖል ተከላ መጠናቀቅን ተከትሎ የመብራት አገልግሎቱን አስጀምረዋል።
አቶ ጎሹ እንዳላማው እንደገለጹት የባህርዳር ከተማን በማዘመን ለጎብኚዎች ለነዋሪዎችና ለኢንቨስትመንት የተመቸች ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ይገኛል።

በዚህም በከተማዋ የሶስት ኪሎ ሜትር የመጀመሪያው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት የአስፋልት፣ የእግረኛና የሳይክል መንገዶችን አሟልቶ መገንባቱን ገልጸዋል።
በተጨማሪም የአረንጓዴ ልማት፣ የመዝናኛ ስፍራዎች፣ ዜጎች ተቀምጠው ጣናን የሚያዩበት መቀመጫዎችንና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን አሟልቶ የተገነባ መሆኑን ተናግረዋል።
ከተማዋን በምሽት ይበልጥ ውብና ማራኪ ለማድረግ የስማርት ፖሎችን ተከላ ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ ዛሬ የመብራት አገልግሎቱ እንዲጀመር መደረጉን ተናግረዋል።

የስማርት ፖሎቹ ከስምንት በላይ የተለያየ ቀለም ያላቸውን መብራቶች የሚያበሩ መሆናቸው ከጣና ሃይቅና ከዘንባባዎቿ ጋር ተዳምሮ ለከተማዋ ተጨማሪ የመስህብ ጸጋ ይዞ መምጣቱን ተናግረዋል።
የስማርት ፖሎቹ ከመብራት ባሻገር ለመኪና፣ ሞባይልና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች ቻርጅ ማድረጊያ የተገጠመላቸው በመሆናቸው ቴክኖሎጂዎችን በቀላሉ መጠቀም የሚያስችል ነው ብለዋል።
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026
አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 14/2018 (ኢዜአ) ፦ በኢትዮጵያ እና በሩሲያ መካከል ያለውን ትብብር በማጠናከር በምርምር፣ በሰው ሃይል ልማት እና በቴክኖሎጂ ሽግግር...
Aug 21, 2026