የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የኮንስትራክሽን ዘርፉ በኢትዮጵያ ስራ እድል ፈጠራ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ነው

May 21, 2025

IDOPRESS

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 12/2017(ኢዜአ)፦የኮንስትራክሽን ዘርፉ በኢትዮጵያ ስራ እድል ፈጠራ ወሳኝ ሚና እየተጫወተ መሆኑን የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ገለፁ።

20ኛው የዓለም ሥራ ድርጅት በሥራ ላይ የተመሰረተ የባለሙያዎች አህጉራዊ ስብሰባ "የማይበገር ማህበረሰብ እና ጤናማ አካባቢ የሰው ኃይልን በብዛት የሚጠቀሙ የኢንቨስትመንት ፕሮግራም አካሄዶች" በሚል መሪ ሀሳብ በአፍሪካ ሕብረት መሰብሰቢያ አዳራሽ እየተካሄደ ነው።


በስብሰባው የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ሀላፊዎች፣ የተለያዩ ሀገራት ተወካዮች፣ የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች ተገኝተዋል።

ከስብሰባው ጎን ለጎንም ሀገራት በሥራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ ያላቸውን ተሞክሮ የሚለዋወጡበት የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

በሥራ ዕድል ፈጠራ ዙሪያ የተካሄደውን ውይይት የመሩት የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል በሰጡት የማጠቃለያ ሀሳብ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ መንግስት ለስራ እድል ፈጠራ ቁርጠኛ ሆኖ እየሰራ ነው።

በተለያዩ ዘርፎች የስራ እድል ለመፍጠር ፖሊሲዎችና መርሃ ግብሮች ተግባራዊ እየተደረጉ መሆኑንም አብራርተዋል።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት እና የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ለሥራ ዕድል ፈጠራ ያላቸውን አቅም በመገንዘብ ትኩረት መደረጉንም ገልፀዋል።

በተለይ መንግስት በስፋት እያከናወነ ያለው የመሠረተ ልማት ዝርጋታ እንደ መንገድ እና ሌሎች ግዙፍ የልማት አውታሮች በኮንስትራክሽን ዘርፍ ከፍተኛ የሥራ ዕድል እየፈጠሩ ነው ብለዋል።

ለአብነትም በአዲስ አበባ ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ሥራዎች በሥራ ዕድል ፈጠራ አይተኬ ሚና እየተጫወቱ እንዳሉ አንስተዋል።

የኮንስትራክሽን ዘርፉ ለሀገር ዕድገት ከሚያበረክተው አስተዋፅኦ ባሻገር በስራ ዕድል ፈጠራ ድርሻው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።

ዘርፉም በኢትዮጵያ እያደገ መሆኑን ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ ማረጋገጥ እንደሚችሉም አንስተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026