
አዲስ አበባ፤ ግንቦት 26/2017(ኢዜአ)፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በጎንደር ከተማ በከፊል የተጣራ የአኩሪ አተር ዘይት የሚያመርተውን የቲቲኬ ኢንደስትሪን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጎንደር ከተማ እየተከናወኑ ያሉ የልማት ስራዎችን ለመጎብኘት ጎንደር ከተማ ገብተዋል።
ጎንደር አፄ ቴዎድሮስ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ፣ የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና የከተማዋ ህዝብ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በከተማዋ በከፊል የተጣራ የአኩሪ አተር ዘይት የሚያመርተውን የቲቲኬ ኢንደስትሪን መርቀው ስራ አስጀምረዋል።
ኢንደስትሪው በ374 ሚሊዮን ብር የተገነባ ሲሆን በቀን 120 ቶን የአኩሪ አተር ዱቄት እና በከፊል የተጣራ የምግብ ዘይት የማምረት አቅም እንዳለውም ተገልጿል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቲቲኬ ኢንደስትሪ ፋብሪካ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለጀመርነው የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት አንድ ሁነኛ አብነት ነው ብለዋል።
ጎንደር ሰላምን በማስጠበቅና በማጽናት ልማትን የማረጋገጥ ለዕድገትም የመትጋት ደማቅ ማሳያ እንደሆነች ተናግረዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026