
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 13/2017(ኢዜአ)፦ ለከተሞች አስተማማኝ ኃይል ተደራሽ ለማድረግ መሰረተ ልማቶችን የማሻሻልና የመቀየር ስራ እየሰራ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገለጸ፡፡
ተቋሙ አገልግሎቱን በማዘመን የኤሌክትሪክ መቆራረጥን ለመቀነስና ፍትሃዊ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በሚያደርገው ጥረት ቅንጅታዊ አሰራር መፍጠር የሚያስችል የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎቸ ጉብኝትና የሚዲያ ፎረም አካሂዷል።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የፕሮሰስና ጥራት ማኔጅመንት ስራ አስፈፃሚ እሱባለው ጤናው እንደገለጹት፤ የኤሌክትሪክ መቆራረጥን ለማስቀረት በዋነኝነት መሰረተ ልማቶች ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ ነው።

እንዲሁም አገልግሎት አሰጣጡን በቴክኖሎጂ መደገፍ አንዱ መሆኑ አንስተው፤ ይህም ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑ ጠቅሰዋል።
በዚህም ካሁን ቀደም በዘርፉ የነበሩ ተግዳሮቶች እየተሻሻሉ መምጣታቸውን ጨምረው ጠቁመዋል፡፡
ተቋሙ አራት መሰረታዊ ነገሮች ላይ ያተኮረ የሪፎርም ስራ እያከናወነ መሆኑን የገለጹት አቶ እሱባለው፤ በዚህም ውጤቶች ታይተዋል ብለዋል፡፡
አሁን ላይ በበርካታ ከተሞች የኤሌክትሪክ ተደራሽነትንና የአገልግሎት ጥራትን ለማሻሻል በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም ነው የተናገሩት፡፡
የኤሌክትሪክ መቆራረጥን ለማስቀረት የተጀመረው ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረገ አሰራር ማህበረሰቡ እንዲያውቀው ለማድረግና ብልሹ አሰራሮችን ለማጋለጥ የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ሚና የላቀ ነው ብለዋል።
የአገልግሎቱ የኮሙኒኬሽን ዘርፍ ስራ አስፈፃሚ አንዋር አብራር በበኩላቸው፤ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማትን ከስርቆት ለመጠበቅ የማህበረሰቡ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።
መገናኛ ብዙሃንም በማህበረሰቡ ዘንድ ግንዛቤ ከመፍጠር አኳያ የበኩላቸውን ሊወጡ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
አገልግሎቱ ከመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ጋር ተቀራርቦ ለመስራት ጉብኝት ማዘጋጀቱንና ለስራው መሳለጥ የሚድያ ፎረም ማቋቋም ማስፈለጉን በዚሁ ወቅት ተገልጿል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026