የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የሐረርን ገጽታ የሚያጎለብቱና የሀዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ ስራዎች እየተከናወኑ ነው - አቶ ኦርዲን በድሪ

Jun 23, 2025

IDOPRESS

ሐረር፤ ሰኔ 15/2017(ኢዜአ)፦ የሐረርን ገጽታ የሚያጎለብቱና የሀዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎች በተጠናከረ መልኩ እየተከናወኑ መሆኑን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዓለም አቀፍ ቅርስ ጀጎል የተገነቡ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ግንባታና ሌሎች ስራዎችን ተመልክተዋል።


እንዲሁም የግንባታ ስራው በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘውን የአባድር ፕላዛ የኮሪደር ልማት ስራ ጨምሮ የገበያ ማዕከላት፣ የመንገድ፣ የኢንቨስትመንትና ሌሎች እየተከናወኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ወቅት እንዳሉት በክልሉ ውጤታማና የህዝቡን ተጠቃሚነት ያረጋገጡ የልማት ስራዎች ተከናውነዋል።

በክልሉ የተከናወኑ የኮሪደር ልማትና ሌሎች የፕሮጀክት ግንባታዎች የከተማዋን ገጽታ የቀየሩና የህዝቡን የመሠረተ ልማት ጥያቄዎች የመለሱ መሆናቸውን ተናግረዋል።

በተለይ በኮሪደር ልማት የተከናወነው ስራ ከተማዋን የበለጠ የቱሪስት መዳረሻነት አጉልቶ ያሳየ መሆኑንም አመላክተዋል።


በአሁኑ ወቅትም የክልሉን ገጽታ የሚያጎለብቱና የህዝቡን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የልማት ስራዎች በተጠናከረ መልኩ እየተከናወኑ መሆኑን ገልጸዋል።

በከተማው ግንባታው እየተጠናቀቀ የሚገኘው የአባድር ፕላዛ የኮሪደር ልማት በተሻለ ጥራትና ፍጥነት እየተከናወነ መሆኑን አመልክተዋል።

በተጨማሪም በክልሉ የተገነቡት የገበያ ማዕከላት ህገ-ወጥና የጎዳና ላይ ንግድን በመከላከል አርሶ አደሩ ምርቱን በቀላሉ ወደ ገበያ በማውጣት ለህብረተሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያቀርብ የሚያስችሉ መሆኑን ገልጸዋል።

በክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙ ፕሮጀክቶች በታቀደላቸው ጊዜ ተጠናቀው ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆኑ መረባረብ ይገባል ብለዋል።

በጉብኝቱ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ሮዛ ኡመርን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026