
አዲስ አበባ፤ ሰኔ 16/2017(ኢዜአ)፦ በዓለም ላይ የሚስተዋሉ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን መቋቋምና ፈጣን ምላሽ መስጠት የሚችሉ ጠንካራ ተቋማትን መፍጠር እንደሚገባ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊ እና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ ገለጹ።
ኢትዮጵያ ከሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት በትይዩ ያስተናገደቻቸው 10ኛው የአፍሪካ ሕብረት አባል ሀገራት የመንግሥት አገልግሎትና አስተዳደር እና የተመድ የአፍሪካ ቀጣናዊ ፎረም ዛሬ ተጠናቀዋል።

የመንግሥት ተቋማት ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን ተቋቁመውና በየዘመኑ እየተንከባለሉ የመጡ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን በመፍታት አካታች፣ ዘላቂ ልማት የሚያመጣ ተጠያቂነትን የሚያሰፍን፣ ሰብዓዊ መብት የሚያከብር፣ የህዝቦችን ትብብር የሚያጠናክሩ ተቋማትን ለመፍጠር ያለመ ነበር።
አቶ አደም ፋራህ በማጠቃለያ መርሀ ግብሩ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በትይዩ የተካሄዱት ሁለቱም መድረኮች በስኬት መጠናቀቃቸውን ገልጸዋል።
በዓለም ላይ እየተስተዋሉ ያሉ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን መቋቋምና ቀድሞ ምላሽ መስጠት የሚችሉ ጠንካራ ተቋማትን መፍጠር ይገባል ብለዋል።
በመሆኑም ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ያለውን ውስብስብነት ከግምት ያስገቡ አዳዲስ ፈጠራዎችና ሞዴሎችን ገቢራዊ ማድረግ ይገባል ነው ያሉት።
የመንግሥት አገልግሎት በአፍሪካ ለዘመናት የቆዩ ችግሮችን መፍታት የሚያስችል መሆኑን በመጥቀስ፤ በአገልግሎት ሰጪዎች ላይ የክህሎት፣ የአመራር እና የትብብር አቅምን ማጎልበት ለሀገራዊ ሽግግር ወሳኝ መሆኑንም አንስተዋል።
የኮንፍረንሱ ዓላማ የተቋም ግንባታ ብቻ ሳይሆን ለዜጎች ግልፅና ቀልጣፋ አገልግሎት የመስጠት ሀላፊነት ጭምር መሆኑን ተናግረዋል።
የመሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ፅንሰ ሀሳብ ለዜጎች ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ከመስጠት የመነጨ መሆኑን ጠቅሰው፤ እስካሁን ባለው ሂደት ተጨባጭ ውጤት መመዝገቡን ገልጸዋል።
የኢትዮጵያ ሪፎርም ከአፍሪካ ሕብረት አጀንዳ 2063 እና የተመድ 2030 ዘላቂ የልማት ግቦች ጋር የተሰናሰነ መሆኑን አንስተዋል።
ስብሰባው የመንግሥት አሰራርን በቴክኖሎጂ መደገፍ፣ የሰው ሀይል አስተዳደርንና የኢኖቬሽን አገልግሎትን ማቀላጠፍ ዘመኑ የሚጠይቀውን ተቋም ለመፍጠር ያግዛል ብለዋል።
ከዚህም ባለፈ ጠንካራ ተቋማዊ አደረጃጀት በመፍጠር ተቋማዊ ተጠያቂነትን ማስፈንና የተሟላ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ ልምዶች የተገኙበት መሆኑንም ገልጸዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026