
ሐመር-ዲመካ፤ ሐምሌ 3/2017 (ኢዜአ)-በደቡብ ኦሞ ዞን አርብቶ አደሩ በራስ አቅም የምግብ ዋስትናውን የሚያረጋግጥበት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን የዞኑ አስተዳደር አስታወቀ።
በዞኑ የ2017/18 ምርት ዘመን የመኸር እርሻ ንቅናቄና የአመራር አባላት የአቅም ግንባታ መድረክ በዞኑ በዲመካ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ ላይ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማዕከል ማሊኮ እንደገለጹት መንግስት በአርብቶ አደሩ አከባቢ የተረጅነት አመለካከትን በመቀየር ወደ ምርታማነት ለማሸጋገር ሰፋፊ የግብርና ልማት ስራዎችን እያከናወነ ነው።
አርብቶ አደሩ ቀደም ሲል መተዳደሪያው በከብት እርባታ ላይ ብቻ የተመሰረተ መሆኑን አንስተው፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መንግስት በሰጠው ትኩረት ከከብት እርባታው ጎን ለጎን በመስኖ ልማት ተሳትፎ እንዲያደርግ እገዛ እያደረገ መሆኑን አንስተዋል ።

ዝናብ አጠር በሆኑ አካባቢዎች የመስኖ አውታሮችን በማስፋፋት ምርታማነትን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል ።
"በዚህም በዞኑ ባለፉት አመታት በተከናወኑ የግብርና ልማት ስራዎች አርብቶ አደሩ የምግብ ዋስትናውን ከማረጋገጥ ባለፈ የኢኮኖሚ አቅሙን የሚያጎለብትበት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል" ብለዋል።
አርብቶ አደሩ በመስኖ ልማት እያደረገ ያለው ተሳትፎ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን የተናገሩት ደግሞ የዞኑ ግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ ምንላርገው አዲሱ ናቸው።

በዞኑ በተከናወኑ የግብርና ልማት ስራዎች የተረጅነት አመለካከት እየተቀረፈ መምጣቱን ተናግረዋል ።
በአሁኑ ሰአት በዞኑ ሰፋፊ የግብርና ልማት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን አንስተው ጥጥ፣ ሙዝ፣ ማሾና ሰሊጥ የመሳሰሉ የግብርና ምርቶችንም ለማዕከላዊ ገበያ ከማቅረብ ባለፈ ወደ ጎረቤት ሀገራት ለገበያ እየተላኩ መሆኑን አስታውቀዋል ።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026