
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 6/2017(ኢዜአ)፦ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ እስካሁን ከ19 ነጥብ 1 ሚሊየን በላይ ነዋሪዎች መመዝገባቸውን የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የህግና ፖሊሲ ዘርፍ ኃላፊ ጋብሬላ አብርሃም ገለጹ።
በኢትዮጵያ የነዋሪዎችን የመታወቅ መብት ለማረጋገጥ፣ በአገልግሎት ሰጭና ተቀባዮች መካከል መተማመን እንዲዳብር፣ በሀገር አቀፍ ደረጃ ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና የተሳለጠ አሰራር ለመዘርጋት የዲጂታል መታወቂያ ገቢራዊ ተደርጓል፡፡
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም የህግና ፖሊሲ ዘርፍ ኃላፊ ጋብሬላ አብርሃም ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት በአዲስ አበባ እና በክልል የዲጂታል የመታወቂያ ምዝገባ ማከናወንና ከተቋማት ጋር ትስስር መፍጠር በትኩረት እየተሰራ ይገኛል ፡፡
ይህንን ተከትሎ እስካሁን 19 ነጥብ 1 ሚሊዮን ነዋሪዎች ለፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ መመዝገባቸውንና ከ55 ተቋማት ጋር ትስስር መፍጠር መቻሉን ተናግረዋል ፡፡

በ2018 በጀት አመት የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን የበለጠ ለማሳደግ እቅድ መያዙንና ከተቋማት ጋር ያለውን ትስስር ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰራም ጠቁመዋል፡፡
በተለይ በክልሎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን ይበልጥ ለማስፋት ከተቋማት ጋር ያለውን ትስስር ለማጠናከር ትኩረት መደረጉን ተናግረዋል፡፡
በተጠናቀቀው በጀት አመት በክልሎች የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባን በተመለከተ ሰፊ የግንዛቤ ስራ መሰራቱን እና በዚህም ውጤት መገኘቱንም አስታውቀዋል።

ለዚህ ከከፍተኛ አመራሩ ጀምሮ ለስራው ትኩረት ሰጥቶ ህብረተሰቡ የዲጂታል መታወቂያ እንዲመዘገብ በማድረግ በኩል ትልቅ ተግባር ተከናውኗል ብለዋል፡፡
በአዲስ አበባ ትምህርት ማህበረሰቡ የፋይዳ ዲጂታል ትግበራ በትምህርት ቤቶች ውጤታማ እንዲሆን ያከናወነውን ተግባር በተሞክሮነት ወደ ክልሎች የማስፋት ስራ እየተሰራ መሆኑን ዳይሬክተሯ አስታውቀዋል፡፡
እንደ ዳይሬክተሯ ገለጻ የዲጂታል መታወቂያ ስርዓት የዲጂታል አገልግሎቱን ለማሳለጥና ጠንካራ የሆነ የማንነት አስተዳደር ስርዓት ለመፍጠር እያገዘ ይገኛል፡፡
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026