የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በዞኑ የስራ እድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች ምርትና አገልግሎታቸውን ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ እየሆኑ ነው

Jul 15, 2025

IDOPRESS

ነገሌ ቦረና፤ ሐምሌ 7/2017(ኢዜአ)፡- በምስራቅ ቦረና ዞን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የስራ እድል የተፈጠረላቸው ወጣቶች ምርትና አገልግሎታቸውን ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ እየሆኑ እንደሚገኙ ተገለጸ።

በዞኑ የስራ እድል ፈጠና ክህሎት ጽህፈት ቤት የስራ እድል ፈጠራ ቡድን መሪ አቶ ጎዳና ሳራ፤ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በዞኑ ለ42ሺህ ወጣቶች የስራ እድል መመቻቸቱን ለኢዜአ ተናግረዋል።


ከእነዚህም መካከል ከ10ሺህ 560 በላይ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ሰልጥነው የተመረቁ ናቸው ብለዋል፡፡

ነገሌ ቦረና ከተማ አስተዳደርን ጨምሮ አጠቃላይ በዞኑ ወደ ስራ ከገቡት ወጣቶች መካከል 15ሺህ 971 ሴቶች እንደሆኑም አንስተዋል፡፡

ወጣቶቹ ወደ ስራ የገቡት በግብርና፣ በአገልግሎትና በማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ሲሆን፤ ግንባታ፣ ንግድ፣ እንስሳት እርባታ፣ ማዕድን ፍለጋና ግብይት፤ የቤትና የቢሮ እቃዎች ማመርተ ሰፊውን ድርሻ ይወስዳሉ ብለዋል።

ወደ ስራ ለገቡት ወጣቶች 78 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ብድር በማመቻቸት ትራክተር፣ ከ10 ሄክታር በላይ የማምረቻ እና መሸጫ ቦታና 61 የመሸጫ ሱቆች ድጋፍ መደረጉን አስታውቀዋል፡፡


ወደ ስራ የገቡ ወጣቶችምምርትና አገልግሎታቸውን በብዛትና በጥራት ለገበያ በተመጣጣኝ ዋጋ እያቀረቡ ተጠቃሚ በመሆን ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

የነገሌ ቦረና ከተማ ነዋሪ አልዬ ዋቆ ከ3 ባልደረቦቹ ጋር በልብስ ስፌትና የአልባሳት ምርት አቅርቦት ስራ ከተሰማሩ ወጣቶች መካከል አንዱ ሲሆን፤አልባሳቱ ባህልን ከማስተዋወቅ ባለፈ በገበያ አዋጭ በመሆኑ የተሻለ ገቢ የሚያስገኝ ተመራጭ የስራ ዘርፍ መሆኑን ገልጿል፡፡

በውጤቱም እራሳችንንና ቤተሰቦቻችንን ከመርዳት አልፈን ከንግድ ስራው የምናገኘውን ትርፍ መቆጠብ ጀምረናል ሲልም ተናግሯል፡፡

ሌላው የከተማው ነዋሪ ወጣት ቢኒያም አምሳሉና 2 ባልደረቦቹ በብረታ ብረት የስራ ዘርፍ የተሰማሩ ናቸው።

ወጣት ቢኒያም በሰጠው አስተያየት፤ ምርታችንን በጥራት እያመረትን ለነገሌ ቦረና ከተማ ህዝብና ለሴክተር መስሪያ ቤቶች ጭምር እያቀረብን ነው ብሏል።

አሁን ላይ ካፒታላቸው 150ሺህ ብር መድረሱን ገልጸው በቀጣይም ስራቸውን ለማስፋፋት ተጨማሪ ብድር ለመውሰድ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026