
ደሴ ፤ ሐምሌ 10/2017(ኢዜአ)፡-በደቡብ ወሎ ዞን በተያዘው የመኸር ወቅት ከ221 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በስንዴ ለማልማት የዘር ሥራ መጀመሩን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ።
በስንዴ ከሚለማው መሬት ከዘጠኝ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ይጠበቃል።
በዞኑ ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ቡድን መሪ አቶ ይመር ሰይድ ፤ በዞኑ ያለው የአየር ንብረትና መልክአምድር ስንዴን በስፋት ለማምረት የተመቸ መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል።
በዚህም በምርት ዘመኑ እርሻ ማሳውን ደጋግሞ በማረስና የግብዓት አቅርቦት ዝግጅት በማድረግ ከ221 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በስንዴ ለማልማት የዘር ሥራ መጀመሩን አስታውቀዋል።
ከሚለማው መሬትም 145 ሺህ ሄክታር የሚሆነው በኩታ ገጠም ጠቁመው፤ ይህም ግብዓት ለማቅረብ፣ ለድጋፍ፣ በጋራ ለመዝራትና ተባይ ለመከላከል ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል ብለዋል።

ከስንዴ ልማቱም ከዘጠኝ ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ ገልጸው፤ አርሶ አደሩ በምግብ ራሱን ከመቻል ባሻገር ለገበያ የሚቀርብ ትርፍ ምርት እንዲያመርት እየተበረታታ መሆኑን አመልክተዋል።
አርሶ አደር አሊ የሱፍ በዞኑ ከለላ ወረዳ የ02 ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ፤ ከአንድ ሄክታር የሚበልጥ መሬታቸውን በኩታ ገጠም ስንዴ ለማልማት የዘር ሥራ መጀመራቸው ገልጸዋል።
ለስንዴ ልማት በቂ ማዳበሪያ ከማግኘታቸው ባለፈ የግብርና ባለሙያዎች ድጋፍ እያደረጉላቸው መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህም የተሻለ በማምረት ከራሳቸው አልፎ ለገበያም ለማቅረብ እየሰራሁ ነው ብለዋል።
በግብርና ባለሙያ ታግዘው የስንዴ ዘር ሥራ መጀመራቸውን የተናገሩት ደግሞ በመቅደላ ወረዳ የ06 ቀበሌ አርሶ አደር አብዱ ኑርዬ ናቸው።
ከግማሽ ሄክታር በላይ መሬት በስንዴ በማልማት የምግብ ዋስትናቸውን ከማረጋገጥ ባለፈ ለገበያ የሚተርፍ ምርት ለማምረት ጠንክረው እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
የኩታገጠም ልማት ግብዓት ቅድሚያ ማግኘታቸው፣ በባለሙያ መደገፋቸውና በጋራ በመዝራት ሰብል መንከባከብ እንዲችሉ ምቹ መደላድል እንደፈጠረላቸው አርሶ አደሮቹ ተናግረዋል።
በደቡብ ወሎ ዞን በ2017/2018 የመኸር ወቅት በአጠቃላይ 432 ሺህ ሄክታር መሬት በተለያዩ ሰብል በማልማት 15 ሚሊዮን ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ከግብርና መምሪያው የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026