
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 12/2017 (ኢዜአ):-የስታርት አፕ አዋጅ የዜጎችን የፈጠራ ሃሳብ ወደ ተጨባጭ ውጤት ለመቀየር የሚያስችል መሆኑን የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ተናገሩ።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባለፈው ሀሙስ ባካሄደው 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ የስታርትአፕ አዋጅን ማፅደቁ ይታወቃል።
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) የአዋጁን መፅደቅ አስመልክተው ለኢዜአ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በማብራሪያቸው ኢትዮጵያ የብዙሃ ዘርፍ የኢኮኖሚ ግንባታ በመንደፍ እየሰራች መሆኑን አንስተው በዚህም ስኬቶች መመዝገባቸውን ተናግረዋል።
የፈጠራ ሃሳቦችም እንደ ሌሎች ዘርፎች ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ መሰረት እንዲሆኑ ለማስቻል አዋጅ መዘጋጀቱን ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
አዋጁ ምቹ የስታርትአፕ ስነ-ምህዳርን በመፍጠር ለዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታው መሰረት እንዲሆን ለማድረግ እንደሆነ ተናግረዋል።
በሌላ በኩልም ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ያላቸውን እምቅ አቅም የበለጠ አውጥተው ለሀገር እድገት እንዲያውሉ አስፈላጊ በመሆኑ አዋጁ መዘጋጀቱንም አብራርተዋል።
የጸደቀው አዋጅ የስታርትአፕ ስነ -ምህዳሩን ለማጎልበት የሚያስችል ምቹ ሁኔታን እንደሚፈጥርም ነው ሚኒስትሩ የተናገሩት።
በዘርፉ ያሉ ተግዳሮቶችን በመፍታት ሃሳብ ያላቸው ወጣቶች እድሎችን በአግባቡ እንዲጠቀሙ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።
ዜጎች ያላቸው ሃሳብ ወደ ተጨባጭ ውጤት እንዲቀይሩ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ሰለመሆኑን ሚኒስትሩ አብራርተዋል።
ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የስታርትአፕ ስነ ምህዳር ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችል መሆኑን ተናግረው፤ ግዙፍ የሆኑ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን ለመፍጠር የሚያስችል አዋጅ መሆኑንም ገልጸው፤ ለሀገር የሚያበረክተው አስተዋፅኦም ከፍተኛ በመሆኑ ለውጤታማነቱ በትኩረት እንደሚሰራ አረጋግጠዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026