
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 11/2017(ኢዜአ)፦ የ2017 በጀት ዓመት የኢትዮጵያ የማንሠራራት ዘመን መነሻ የሆኑ ውጤታማ ተግባራት የተከናወኑበት ዓመት መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ፡፡
በ2018 በጀት ዓመትም በሁሉም ዘርፎች የተገኙ ውጤቶችን ለማስቀጠልና በጠንካራ መሠረት ላይ የማጽናት ስራዎች እንደሚከናወኑ ጠቁመዋል፡፡
የፌደራል ተቋማት የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ከፌደራል ተቋማት አመራሮች ጋር ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ የ2017 በጀት ዓመት በብዙ መልኩ የኢትዮጵያ የብልጽግና ታሪክ እጥፋት የተመዘገበበት ዓመት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በጀት ዓመቱ በሁሉም መስኮች የኢትዮጵያ የማንሠራራት ዘመን መነሻ እንደነበር አንስተው ስኬታማና የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም የተከናወነበት ዓመት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በውጤቱም በአምራች፣ በግብርና፣ በአገልግሎትና በማዕድን እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ታሪካዊ አፈጻጸሞች መመዝገባቸውን ጠቁመዋል፡፡
በከተሞች እየተከናወኑ የሚገኙ የኮሪደርና ሌሎች ልማቶች ውጤት ማምጣት መጀመራቸውን ጠቁመው፤ በትምህርት፣ በጤና፣ በፍትሕና አስተዳደር እንዲሁም በዲፕሎማሲው መስክ አመርቂ ውጤቶች እንደተመዘገቡ አብራርተዋል፡፡
ኢትዮጵያ በአመቱ ከ150 በላይ ዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ኮንፍረንሶችን በማስተናገድ ለቱሪዝም የተመቸች መዳረሻ መሆኗን በተግባር ማስመስከሯንም ገልጸዋል፡፡

በአዲሱ በጀት ዓመት ዕቅድ ባለፈው ዓመት በጠንካራ የሪፎርምና የዕቅድ አተገባበር የተገኙትን የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የዋጋ ማረጋጋት፣ የሀገር ውስጥ ገቢ መሰብሰብ እና የወጪ ንግድ ዕድገትን የበለጠ ለማጠናከር በትኩረት እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡
ከማክሮ ኢኮኖሚ እና ከአምራች ዘርፎች አኳያም የተመዘገቡ መልካም ጅምሮችን የማስቀጠልና በጠንካራ መሠረት ላይ የማጽናት ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል፡፡

የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ(ዶ/ር) በበኩላቸው ኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ ውጤታማ ስራዎችን በማከናወን ላይ ትገኛለች ብለዋል፡፡
በዚህም ምርትና ምርታማነትን ከማሳደግ አኳያ ውጤታማ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆናቸውን ጠቁመው፤ በአዲሱ በጀት ዓመትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡
በተያዘው በጀት ዓመት በተለይም ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ፣ የስራ ዕድል በሰፊው መፍጠር፣ የኑሮ ውድነትንና የዋጋ ግሽበትን ትርጉም ባለው መልኩ መቀነስ፣ ገቢ የመሰብሰብ፣ ኤክስፖርት የማስፋት ስራዎችን በውጤታማነት በማከናወን ሪፎርሙን በስኬት ለማስቀጠል እንደሚሰራም ተጠቁሟል፡፡
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026