
አዲስ አበባ፤ሐምሌ 15/2017(ኢዜአ)፦በ2017 በጀት አመት ህብረተሰቡ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ገለፀ።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በመንግስትና በህብረተሰብ ተሳትፎ የተገነባ መሆኑም ተገልጿል።
በ2017 በጀት ዓመት ህብረተሰቡ ለግድቡ ግንባታ ያደረገውን ድጋፍ፣ ትብብርና እገዛ በተመለከተ የጽህፈት ቤቱ ምክትል ስራ አስፈጻሚ ፍቅርተ ተአምር ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸው የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የተፋሰሱ ሀገራት ህዝቦችን በጋራ የማደግ ትልምን የሚያሳካ ፕሮጀክት መሆኑንም ተናግረዋል።
በዚህም መላው ኢትዮጵያውያን በሞራል፣ በገንዘብ፣ በጉልበት፣ በፐብሊክ ዲፕሎማሲ እንዲሁም አካባቢ ጥበቃ ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ያሳኩት ዘመን ተሻጋሪ ስኬት መሆኑንም አስረድተዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከኢትዮጵያ አልፎ የአካባቢውን ሀገራት የኤሌትሪክ ሃይል ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት መሆኑንም አክለዋል።
ምክትል ስራ አስፈፃሚዋ ከቦንድ ሽያጭና ስጦታ፣ ከዲያስፖራው ማህበረሰብ፣ ከ8100 A አጭር የፅሁፍ መልዕክት ድጋፉ መሰባሰቡንም ጠቅሰዋል።
በዚህም በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ለግድቡ ግንባታ 1 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር መሰብሰቡን ገልጸው፤ ይህም ከዕቅዱ አንጻር የ7 በመቶ ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል፡፡
ህብረተሰቡ ያደረገው ድጋፍ ከባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር አፈፃፀሙ የ21 በመቶ ብልጫ ማሳየቱንም ጠቅሰዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026