
ሆሳዕና፤ሐምሌ 15/2017(ኢዜአ)፡-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በየዘርፉ የሕዝቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው(ዶ/ር) ገለጹ።
"ከመስፈንጠር ከፍታ ወደ ላቀ እመርታ!” በሚል መሪ ሀሳብ የተዘጋጀ የመንግሥትና የፓርቲ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ያተኮረ የአመራር ምክክር መድረክ በሆሳዕና ከተማ ተካሂዷል፡፡

በመድረኩ ላይ ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳመለከቱት፤ ባለፈው የበጀት ዓመት የማህበረሰቡን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተያዙ እቅዶችን በቅንጅት በመስራት ተስፋ ሰጪ ውጤት ተመዝግቧል፡፡
በዚህም ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የኑሮ ውድነትን ከማረጋጋት ባሻገር በከተማና በገጠር መንገድ ተደራሽ እንዲሆን የተደረገውን ጥረት ጠቅሰዋል።
ለወጣቶች የስራ እድል ከመፍጠር አንጻር የተከናወኑ ተግባራት ውጤታማ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ይህም በክልሉ በበጀት ዓመቱ የሕዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስራዎች በትክክለኛ መንገድ ላይ እንደሚገኙ አንስተዋል።
በተያዘው የበጀት ዓመት መልካም አስተዳደርን በማስፈን ፍትሀዊና ቀልጣፋ አገልግሎት ለተገልጋዩ ለመስጠት ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራም ተናግረዋል።
የተገኙ ስኬቶችን አጠናክሮ በማስቀጠል በየዘርፉ የሕዝቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማሳደግ አመራሩ በቅንጅት መስራት እንዳለበትም አሳስበዋል፡፡
በብልፅግና ፓርቲ የክልሉ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ዲላሞ ኦቶሬ (ዶ/ር)፥ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በፓርቲ ደረጃ ተጨባጭ ውጤት ለማስመዝገብ በቅንጅት ሲሰራ ቆይቷል ብለዋል፡፡
በዚህም በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።
ባለፈው የበጀት ዓመት የተስተዋሉ ውስንነቶችን በማረም የሕዝብ ተጠቃሚነትን ይበልጥ ለማጎልበት በትኩረት መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
ከመድረኩ ተሳታፊዎች መካከል የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዘይኔ ቢልካ እንዳሉት፤ በዞኑ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት በግብርና ልማት፣ በንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና በሌሎችም ዘርፎች ውጤታማ ስራዎች ተከናውነዋል።
በመድረኩ ላይ ካለፈው የስራ ዘመን እቅድ አፈጻጸም ሌላ የ2018 በጀት ዓመት የትኩረት አቅጣጫ ላይ ምክክር የተደረገ ሲሆን ፤ በዚህም የክልል፣ የዞን፣ የልዩ ወረዳና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026