የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

የክልሉ ምክር ቤት በክትትልና ድጋፍ ተግባሩ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያጎለበቱ ሥራዎች እንዲከናወኑ ሰርቷል

Jul 24, 2025

IDOPRESS

ወልቂጤ፣ ሐምሌ 16/2017 (ኢዜአ)፡-‎የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በክትትልና ድጋፍ ተግባሩ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ያጎለበቱ የልማት ሥራዎች እንዲከናወኑ መስራቱን የምክር ቤቱ ዋና አፈ-ጉባኤ ፋጤ ስርሞሎ ገለጹ።

‎ምክር ቤቱ 6ኛ ዙር 4ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤውን በወልቂጤ ከተማ ማካሄድ ጀምሯል ።


በጉባኤ መክፈቻው ላይ ንግግር ያደረጉት ‎የክልሉ ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ ፋጤ ስርሞሎ እንደገለፁት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ምክር ቤቱ ተከታታይነት ያለው መደበኛ እና ድንገተኛ የክትትል፣ የቁጥጥርና ድጋፍ ሥራዎች ሲያከናውን ቆይቷል።

በዚህም በክልሉ በፖለቲካዊ፣ በማህበራዊና በኢኮኖሚያዊ ዘርፎች ላይ የተሻለ ለውጥ እንዲመጣ የሚጠበቅበትን ኃላፊነት ሲወጣ መቆየቱን አንስተዋል።

የመንገድ፣ የውሃ፣ የመስኖ እና የጤናን ጨምሮ ሌሎች ማህበራዊ ተቋማት ተግባርን የመከታተል፣ የማረምና የመደገፍ ስራ ማከናወኑንም ተናግረዋል ።

በዓመቱ በክልሉ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን ጀምሮ የመጨረስና የተጓተቱትን አጠናቅቆ ወደ አገልግሎት ከማስገባት አንጻር የተሻለ አፈጻጸምና ልምድ እየታየ መምጣቱን ምክር ቤቱ ማረጋገጡን አንስተዋል።

‎በዚህም ክልሉ ከተመሰረተ አጭር ጊዜ ቢሆንም ተጓተው የነበሩ ሰፋፊ የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ወደ ስራ እንዲገቡ በትኩረት መሰራቱን ነው አፈ-ጉባኤዋ የተናገሩት።

በ‎ቀጣይም ለሰላም ግንባታ፣ ለልማት እና ለመልካም አስተዳደር ሥራዎች ውጤታማነትና ተፈጻሚነት ምክር ቤቱ የክትትልና የቁጥጥር ሥራዎቹን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

ዛሬ በተጀመረው የዓመቱ ማጠቃለያ መደበኛ ጉባኤም ‎ምክር ቤቱ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ እንደሚያሳልፍ አፌ-ጉባኤዋ ጠቁመዋል።

የምክር ቤቱ መደበኛ ጉባኤ ዛሬን ጨምሮ ለሁለት ተከታታይ ቀናት እንደሚካሄድ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026