
ባህር ዳር፣ሐምሌ 16/2017 (ኢዜአ)፡-በደቡብ ጎንደር ዞን ሰላምን በማፅናት ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ተግባራት ምቹ ሁኔታ መፈጠሩን የዞኑ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ አስታወቀ።
የመምሪያው ኃላፊ አቶ ጌትነት በዛ ለኢዜአ እንደገለጹት፤በየደረጃው የሚገኘው የዞኑ ሕዝብ የፅንፈኛውን ቡድን የጥፋት መንገድ አደባባይ ወጥቶ ከማውገዝ ባለፈ የህግ የበላይነት እንዲከበር የድርሻውን መወጣቱን ቀጥሏል።
ተከታታይ ህዝባዊ መድረኮች በመፍጠር ቡድኑን ከሕህዝቡ የመነጠል ስራ መከናወኑን አውስተዋል።
በዞኑ የሰፈነውን ሰላምና መረጋጋት በማስጠበቅ የሕብረተሰቡን የልማት ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያግዙ ውጤታማ ሰራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል።
መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተከትሎ ወደ ሰላም የመጡ በርካታ ታጣቂዎችን የተሃድሶ ስልጠና በመውሰድ ሕብረተሰቡን በልማት እንዲክሱ እየተደረገ ነው ብለዋል።
ፅንፈኛውን ቡድን ከዞኑ ለማፅዳት ከመከላከያ ሰራዊቱና ከሌሎችም የህግ አስከባሪዎች ጋር በመተባበር እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን አንስተዋል።
በተወሰደበት እርምጃ ፅንፈኛው እየታደከመ መምጣቱን ገልጸው፤ ይህም ለግብርና ልማቱ ግብአት ለማቅረብና ባለሙያዎች ተንቀሳቅሰው አርሶ አደሩን እንዲደግፉ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል ብለዋል።
ቀሪ የፅንፈኛውን ቡድን አባላት በየጊዜው የሰላም አማራጭን በመቀበል አሁንም እየተመለሱ መሆኑም አመልክተዋል።
የተገኘውን ሰላም በማፅናት ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የልማት ስራዎችን ይበልጥ ለማጠናከር አስቻይ መደላደል መፈጠሩን ኃላፊው አስታውቀዋል።
መንግስት አሁንም በሰላማዊ መንገድ ለሚመጡ ታጣቂዎች እጁ የተዘረጋ መሆኑን ጠቁመው፤ ይሄን በማይቀበሉት ላይ ደግሞ ከሕዝቡ ጋር በመተባበር የህግ ማስከበር ስራው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026