
አዲስ አበባ፤ ሐምሌ 21/2017(ኢዜአ)፦በሳይንስ ሙዚየሙ ኢትዮጵያ አስደናቂ የሳይንስና የፈጠራ ጉዞ ላይ መሆኗን ተመልክቻለሁ ሲሉ የኩባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆርጌ ሉዊስ ገለጹ።
የኩባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆርጌ ሉዊስ ታፒያ ፎንሴካ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ጋር በመሆን ሳይንስ ሙዚየምን ጎብኝተዋል።
በሙዚየሙ ቋሚ ኤግዚቢሽኑ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ፣ የአየር ንብረት ለውጥ መከላከል፣ የግብርና፣ የውሃና ኢነርጂ እንዲሁም የኤሮስፔስ እና አቪየሽን ማሳያዎችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ሆርጌ ሉዊስ በሳይንስ ሙዚየም ኢትዮጵያ አስደናቂ የሳይንስና የፈጠራ ጉዞ ላይ መሆኗን ተመልክቻለሁ ብለዋል።

አፍሪካ የኋላቀርነት መጥፎ ትርክትን ዘመኑን በዋጀ የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ተጨባጭ ሥራዎች እየቀየረች እንደምትገኝ ኢትዮጵያ ሁነኛ ማሳያ ናት ብለዋል።
ሳይንስ ሙዚየም ከኢትዮጵያ አልፎ አፍሪካ አሁን የደረሰችበትንና የመጪውን ዘመን የቴክኖሎጂ ዘመን ራዕይዋን የሚያሳይ መሆኑን መገንዘባቸውንም ጠቅሰዋል።
ኢትዮጵያ እና ኩባ በቴክኖሎጂው ዘርፍ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያሳድጉ ጉዳዮች ዙሪያ ትብብራቸውን ለማጠናከር በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ተገልጿል፡፡
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026