
አሶሳ፤ ሐምሌ 22/2017 (ኢዜአ)፦ ወጣቶች የኮደርስ ስልጠና በመከታተል የቴክኖሎጂ አቅማቸውን ሊያሳድጉ እንደሚገባ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት አባላት ተናገሩ።
የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና የ5 ሚሊየን ወጣቶችን መሠረታዊ የዲጂታል ክህሎት ለማዳበር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ2016 ዓ.ም የተጀመረ ኢንሼቲቭ ነው።
ኢንሼቲቩ በሁሉም አካባቢዎች እየተተገበረ ሲሆን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልም ከ7 ሺህ በላይ ዜጎች ስልጠናውን በበይነ መረብ እየተከታተሉ መሆኑን የክልሉ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ኤጄንሲ አስታውቋል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አሻደሊ ሀሰን ሰሞኑን በተካሄደው የክልሉ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ የኮደርስ ስልጠና የሀገሪቱን ዲጂታል ኢኮኖሚ ግንባታ የሚያሳልጥ እና ዜጎችን በሁሉም መስክ ተወዳዳሪ የሚያደርግ በመሆኑ ወጣቶች ስልጠናውን እንዲከታተሉ የምክር ቤት አባላት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ መጠየቃቸው ይታወሳል።
በዚሁ ጉዳይ ኢዜአ ያነጋገራቸው የምክር ቤቱ አባላት የኮደርስ ስልጠና ለሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ከሚኖረው አስተዋጾኦ ባለፈ ለግለሰብ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ አስተዋጽኦው የጎላ መሆኑን ገልጸዋል።
ከምክር ቤቱ አባላት መካከል አቶ ኑረዲን ዘካሪያ እንደተናገሩት የኮደርስ ስልጠና እንደ ሀገር የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ውስንነቶችን የሚቀርፍ እና ዘርፈ ብዙ ጠቃሜታ ያለው ነው።
ስልጠናው ሀገሪቱ ከጊዜው ጋር እንድትራመድ የሚያስችል በመሆኑ በተለይም ወጣቶች ለመጪው የረቀቀ የቴክኖሎጂ ዘመን ራሳቸውን ዝግጁ የሚያደርጉበት መልካም አጋጣሚ በመሆኑ ሊጠቀሙበት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
ሌላዋ የምክር ቤቱ አባል የራስወርቅ መሠረት በበኩላቸው የኮደርስ ስልጠና ወጣቶችን ያማከለ ቢሆንም ለማንኛውም ዜጋ የዕለት ተዕለት የስራ እንቅስቃሴ ጠቃሚ የሆነ መርሃግብር መሆኑን ተናግረዋል።

እንደ ምክር ቤት አባሏ ወጣቶች የመርሃግብሩ ተሳታፊ እንዲሆኑ የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመጠቀም ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውንም አመላክተዋል።
በራሳቸውም ስልጠናውን ማጠናቀቃቸውን የገለጹት የምክርቤት አባሏ፤ ከስልጠናው የዲጅታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዘዴዎችን እና በመደበኛ ስራቸው ላይ አጋዥ የሚሆን ዕውቀት ማግኘታቸውን አክለዋል።
የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ ኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ኤጄንሲ ዳይሬክተር አቶ ይታያል በላይ እንዳሉት እስከአሁን ድረስም 7ዐዐ የሚሆኑ ዜጎች ስልጠናውን አጠናቀው የምስክር ወረቀት አግኝተዋል።

በተያዘው በጀት ዓመት ተግባሩንም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
ከበጎ ፍቃድ አገልግሎት ጋር በማስተሳሰር ወጣቱ በክረምት ወቅት ስልጠናውን እንዲከታተል ከተለያዩ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ጋር እየሰራን እንገኛለን ብለዋል ።
ወጣቶች ሀገሪቱ ለያዘችው የዲጅታል ኢኮኖሚ ግንባታ መሠረት የሚሆን የኮደርስ ስልጠና እንዲወስዱ አቶ ይታያል መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
በክልሉ መርሃግብሩ ከተጀመረ ወዲህ ከ7 ሺህ በላይ ዜጎች በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ በዳታ ሳይንስና አርተፊሻል ኢንተለጀንስ መሰረታዊ የዲጂታል ክህሎት ስልጠናውን እየወሰዱ ነው።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026