🔇Unmute
አዲስ አበባ ፤ መስከረም 30/2018 (ኢዜአ)፡- የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣናን ሙሉ ለሙሉ ገቢራዊ ማድረግ ጊዜ የማይሰጠው አንገብጋቢ ጉዳይ ነው ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ ገለጹ።
24ኛው የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ አገራት የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) የመሪዎች ጉባኤ በኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ ነው።
የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር መሐሙድ አሊ ዩሱፍ በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ሁነቶች በአፍሪካ የኢኮኖሚ እድገት እና ተወዳዳሪነት ተጽእኖ እያሳደሩ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ይህም ከመቼው ጊዜ በላይ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ሙሉ ለሙሉ በአፋጣኝ መተግበር እንደሚገባው የሚያመላክት ነው ብለዋል።
ሊቀ መንበሩ የአፍሪካ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች ከቀረጥ ጋር ያልተያያዙ የንግድ ገደቦችን በማንሳት እና በአፍሪካ ሀገራት መካከል የተሳለጠ የንግድ ልውውጥ ማድረግ የሚያስችሉ ማዕቀፎችን በመተግበር ለአጀንዳ 2063 መዋቅራዊ ትራንስፎርሜሽን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል።
የኮሜሳ፣ የደቡብ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ (ሳዴቅ) እና የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ (ኢኤሲ) የሶስትዮሽ ትብብር ማዕቀፍ መሆኑን ጠቅሰው፤ ማዕቀፉ የትስስር አጀንዳ ተምሳሌት እና አንድ የሆነች፣ የበለጸገች እና ራሷን የቻለች አህጉር ለመፍጠር የተጀመረውን ጉዞ የተስፋ ብርሃን ፈንጣቂ መሆኑን ተናግረዋል።
የአፍሪካ ህብረት ከቀጣናዊ የኢኮኖሚ ማህበረሰቦች ጋር ጠንካራ ትብብር በመፍጠር ቀጣናዊና አህጉራዊ የትስስር አጀንዳዎችን ትግበራ ለማፋጠን በቁርጠኝነት እንደሚሰራ መግለጻቸውን ኢዜአ ከህብረቱ ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026