የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ
ግንኙነት
ፈልግ
አንድ ቀበቶ ፣ አንድ መንገድ

በኮሜሳ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ የዲጂታል መሠረተ ልማት ለሀገር በቀል ኢኮኖሚ ዕድገት ቁልፍ ጉዳይ አድርጋ እየሰራች መሆኑን ማስገንዘብ ተችሏል

Oct 11, 2025

IDOPRESS

🔇Unmute

አዲስ አበባ፤ መስከረም 30/2018(ኢዜአ)፦ በምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ሀገራት የጋራ ገበያ(ኮሜሳ) የመሪዎች ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ የዲጂታል መሠረተ ልማት ለሀገር በቀል ኢኮኖሚ ዕድገት ቁልፍ ጉዳይ አድርጋ እየሰራች መሆኑን ማስገንዘብ እንደቻለች የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ገለጹ።

24ኛው የምስራቅና ደቡብ አፍሪካ ሀገራት የጋራ ገበያ(ኮሜሳ) የመሪዎች ጉባኤ ትናንት በኬንያ ናይሮቢ ተካሂዷል።


በጉባኤው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)ን ጨምሮ ከኮሜሳ አባል ሀገራት የተውጣጡ የሀገራት መሪዎች ተሳትፈዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በጉባኤው ባደረጉት ንግግር ዲጂታላይዜሽን የኢትዮጵያ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ አጀንዳ ወሳኝ ምሰሶ መሆኑን አንስተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንደ የኮደርስ ስልጠና ኢኒሼቲቭ ባሉ ጠንካራ የዲጂታል መሠረተ ልማት በመገንባትና ሰፊ ክህሎት ከማፍራት አኳያ ኢትዮጵያ አመርቂ ውጤቶችን በማስመዝገብ ላይ እንደምትገኝ መጥቅሳቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም ተናግረዋል፡፡

እነዚህ ዘርፈ ብዙ ጥረቶች የኢትዮጵያን ዕድገትና ለውጥ ለመምራት ብሎም ጠንካራ ዲጂታል መሠረተ ልማት ለመፍጠር ያላትን ቁርጠኝነት የሚያሳዩ መሆናቸውንም ጠቁመዋል።

ኢትዮጵያ የጀመረችውን የብሔራዊ መታወቂያ ሥርዓትና የመንግሥት አገልግሎቶችን አውቶሜት የማድረግ ተግባራት ለዲጂታል ዘርፉ እድገት እንደ ቁልፍ ምሳሌዎች የሚወሰዱ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

እንደ ኮደርስ ስልጠና ኢኒሼቲቭ ያሉ መርሐ ግብሮች ወጣቶች የዲጂታል ክህሎትን በመታጠቅ እና በዘርፉ ትርጉም ያለው ለውጥ እንዲያመጡ የሚያስችሉ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው የሀገር ውስጥ የዲጂታላይዜሽን ጥረቶች ከፍተኛ ውጤት እንዲያስገኙ ከቀጣናዊ ግቦች ጋር መጣጣም እንደሚገባም መናገራቸውን ኃላፊዋ ገልጸዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ቢልለኔ ስዩም አክለውም፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአፍሪካ ወጣቶች ለአህጉሪቱ ልማትና ዕድገት ወሳኝ ሃብት መሆናቸውን ማንሳታቸውን ጠቅሰዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የአፍሪካ ሀገራት የአህጉሪቱን የጎለበተ የወጣቶች ተሰጥኦ እና አቅም መጠቀም እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት - የኢትዮጵያ ድምጽ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ወቅታዊ፣ ትክክለኛ እና አጠቃላይ የዜና ዘገባዎችን ለማቅረብ የሚሰራ የኢትዮጵያ የዜና ወኪል ነው። ጠቃሚ የሀገር ውስጥ እና አለምአቀፍ ሁነቶችን እንዘግባለን፣ ሀገራዊ ፖሊሲዎችን እና ማህበራዊ ለውጦችን በጥልቀት በመመርመር ለህዝብ፣ ለመንግስት ኤጀንሲዎች፣ ለንግድ ድርጅቶች እና ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ታማኝ የዜና ምንጭ እናቀርባለን። ጋዜጠኞቻችን በአገር ውስጥ እና በውጭ አገር አዳዲስ ዜናዎች እና መረጃዎች በተቻለ ፍጥነት እንዲደርሱ እና ግልጽነትን እና የህዝብ ተሳትፎን ለማስተዋወቅ ነው.

መግለጫ

ታዋቂው ታይም መጽሔት ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ባስነበበው ሰፊ ዘገባው ምን አለ?

በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...

Sep 14, 2026

የኦሮሚያ ክልል ንግድ ቢሮ ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ትኩረት ሰጥቷል

አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...

Sep 7, 2026

የመስኖና የሜካናይዜሽን ሽግግር በኢትዮጵያ ግብርና ዘርፍ ከተመዘገቡት ስኬቶች ዋነኞቹ ናቸው-ምሁራን

ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...

Sep 3, 2026

በአማራ ክልል የጥጥ ምርትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል

ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...

Aug 28, 2026