🔇Unmute
ቡታጅራ ፤ መስከረም 30/2018 (ኢዜአ)፡- የኮሪደር ልማትን ጨምሮ የህዝብን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የተለያዩ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የምስራቅ ጉራጌ ዞን አስተዳደር አስታወቀ።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሙስጠፋ ሀሰን፤ ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታበዞኑ ያለውን እምቅ ሃብት በማልማት የከተማና ገጠሩን አካባቢ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ዘርፈ ብዙ የልማት ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አንስተው በተያዘው ዓመትም በተጠናከረ መልኩ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።
በዞኑ ሰላምን በማፅናት ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ ከተረጅነት ወደ አምራችነትና በዘላቂነት ራስን የመቻል ጥረት ልዩ ትኩረት የተሰጠው መሆኑንም ገልጸዋል።

በዚህም የበጋ የመስኖ ልማትን ጭምር በማጠናከር የማምረት እንዲሁም በከተሞች የኮሪደር ልማት ስራዎች በተጠናከረ መልኩ እየተከናወኑ መሆናቸውን አንስተዋል።
ከኮሪደር ልማት በተጨማሪ የህዝብን ጥያቄዎች መሰረት ያደረጉና ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የተለያዩ የልማት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን አስረድተዋል።

የህዝብን የልማት ጥያቄዎች መሰረት ያደረጉና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የልማት ሥራዎች በስፋት እየተሰሩ መሆኑንም አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

ከቡታጅራ ከተማ ነዋሪዎች መካከል ወጣት እያሱ ታምራት እና አቶ ጌትነት ወረደ፤ የከተማዋ የኮሪደር ልማት ለዘመናዊ የከተማ እድገት መሰረት እየጣለ እና ለብዙዎችም የሥራ እድል እየፈጠረ መሆኑን ገልጸዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026