🔇Unmute
ሆሳዕና ፤ ጥቅምት 4/2018(ኢዜአ)፦መንግስትለግብርናው ዘርፍ በሰጠው ትኩረትና ድጋፍ በምርታማነት ከተረጂነት ለመውጣት እየሰሩ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሞዴል አርሶ አደሮች ተናገሩ፡፡
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ያለፈውን ዓመት አፈጻጸምና የበጀት ዓመቱን የበጋ ወቅት ስራ የሚገመግም መድረክ አካሄዷል።
በመድረኩም በግብርናው ዘርፍ የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ አርሶ አደሮች ሽልማትና የዕውቅና መርሃ ግብር ተካሄዷል።
ከተሸላሚዎቹ መካከል ኢዜአ ያነጋገራቸው ሞደል አርሶ አደሮች በግብርናው ዘርፍ በመንግስት በተሰጠው ትኩረትና ድጋፍ በምርታማነት ከተረጂነት ለመውጣት እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
አርሶ አደሮቹ የሌማት ትሩፋትን ጨምሮ በተቀናጀ የግብርና ልማት ስራ ውጤታማና ተጠቃሚ መሆናቸውን አንስተው የተሰጣቸው እውቅና እና ሽልማትም ለተሻለ ስራ የሚያነሳሳቸው መሆኑን ተናግረዋል።

ከከምባታ ዞን አዲሎ ዙሪያ ወረዳ ሀሚዶ ጎፎሮ ቀበሌ ነዋሪው ሞዴል አርሶ አደር አብነት ዴላሞ የሌማት ትሩፋትን ጨምሮ በተቀናጀ ግብርና ስራ ላይ ተሰማርተው ተጠቃሚ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡
በተቀናጀ የግብርና አሰራር ላይ ያላቸውን ልምድ ለሌሎች አርሶ አደሮች እያካፈሉ መሆኑን ገልፀው በክልሉ መንግስት የተሰጣቸው እውቅና ለተሻለ ስራ እንዲነሳሱ እንደሚያደርጋቸው ተናግረዋል።
የግብርና ባለሙያዎችን ሙያዊ ድጋፍ በትኩረት በመከታተልና ተግባራዊ በማድረግ ውጤታማ መሆናቸውን የገለፁት ደግሞ በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ አቦኮ ቀበሌ ነዋሪው ሞዴል አርሶ አደር ገብሩ ታፈሰ ናቸው።
በቆሎን በክላስተር ከማምረት ጀምሮ የአትክልትና ፍራፍሬ ሰብሎችን መስኖን በመጠቀም በዓመት ሶስት ጊዜ እንደሚያመርቱም ተናግረዋል፡፡

በስልጤ ዞን አሊቾ ውሪሮ ወረዳ ሽልማት ቀበሌ ነዋሪ ሞዴል አርሶ አደር ፈዲላ ጀማል በበኩላቸው በአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም በቅመማ ቅመምና በእንስሳት ተዋፅኦ ምርቶች ላይ በትኩረት እየሰሩ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በተለይም በጥቂት መሬት ላይ የሚያመርቱትን የሮዝመሪ ምርት ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን ገልጸው መንግስት ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት የበለጠ የሚያነሳሳና አርሶ አደሩ የልፋቱን ዋጋ እንዲያገኝ እያደረገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የቢሮው የ2018 የበጋ ወቅት የተቀናጀ የግብርና ልማት ሥራዎች የንቅናቄ መድረክ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና ሞዴል አርሶ አደሮች በተገኙበት በዱራሜ ከተማ መካሄዱ ይታወሳል፡፡
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026