🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 6/2018(ኢዜአ)፡- ኢትዮጵያ ተግባራዊ ያደረገችው የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ለኢንቨስትመንትና ለንግድ ይበልጥ ምቹ ምህዳር መፍጠሩን የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ገለጹ።
5ኛው የፓኪስታን-አፍሪካ የንግድ ልማት ጉባኤና አውደ ርዕይ መክፈቻ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ ተካሂዷል።
በንግድ ልማት ጉባኤውና አውደ ርዕዩ ላይ ከ150 በላይ የፓኪስታን አምራች ድርጅቶች እየተሳተፉ መሆናቸው ተጠቁሟል።

በመክፈቻው መርሐ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ የአፍሪካ መግቢያ በር መሆኗን ጠቅሰው፣ በሀገሪቱ ምቹ የኢንቨስትመንትና የንግድ ምህዳር መኖሩን አስገንዝበዋል።
መንግሥት ቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ በርካታ ሥራዎችን እየሠራ መሆኑንም አመልክተዋል።
ሚኒስትሩ አክለውም፣ በኢትዮጵያ ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮች መኖራቸውን በማንሳት፣ በግብርና፣ በአምራች ኢንዱስትሪና ሌሎችም ዘርፎች ሰፊ አቅም እንዳለ ነው የጠቀሱት።
ኢትዮጵያን ጠንካራ የንግድ ማዕከል ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆኑንና የኢኮኖሚ ልማት ዕድገቷን የሚያስቀጥሉ በርካታ ሜጋ ፕሮጀክቶችን እየገነባች መሆኗን ተናግረዋል።

ከእነዚህም መካከል የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ፣ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚከናወኑ የግብርና ስራዎች፣ የአረንጓዴ አሻራ ተነሳሽነት፣ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክቶች፣ የማዳበሪያ ፋብሪካ ግንባታ ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል።
የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራው ፓኪስታንን ጨምሮ ከሌሎች የዓለም ሀገራት በርካታ ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ኢንቨስት እንዲያደርጉ ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረ ጠቁመዋል።

የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ዴኤታ አብዱልሃኪም ሙሉ(ዶ/ር)፤ ጉባኤው የንግድ ተግዳሮቶችን በመፍታት ብሎም አዳዲስ የንግድና ኢንቨስትመንት መስኮችን ለመፍጠር እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡
በቀጣይ በንግድና ሌሎች አንኳር ስራዎች የተለያዩ ትብብሮችን ለማድረግ እንደሚረዳ ጠቁመው ኢትዮጵያ በሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያው በርካታ ዘርፎችን ይበልጥ ምቹ እንዲሆኑ ማስቻሏን ጠቁመዋል፡፡

በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር አቲፍ ሸሪፍ በበኩላቸው፣ የንግድ ልማት ጉባኤው በፓኪስታን እና በአፍሪካ ሀገራት መካከል ያለውን የኢኮኖሚ አጋርነት ይበልጥ እንደሚያጠናክር ገልጸዋል።
በጉባኤውና በተዘጋጀው አውደ ርዕይ ከ150 በላይ የፓኪስታን ኩባንያዎች መሣተፋቸውን ጠቅሰው፣ ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት የሚካሄድ መሆኑንም አረጋግጠዋል።
በአውደ ርዕዩ የሕክምና መድኃኒት ምርትና መሣሪያዎች፣ የውበትና የቆዳ እንክብካቤ ውጤቶች፣ የጨርቃጨርቅና አልባሳት ምርቶች፣ የምግብና የምግብ ነክ የግብርና ምርቶች፣ የአውቶሞቲቭ መለዋወጫና ሌሎችም ምርቶች ቀርበዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026