🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ ህዳር 2/2018(ኢዜአ)፦ የብራውን ፉድ ፋብሪካ የአርሶ አደሮችን የግብርና ምርታማነት በመጨምር የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትን እንደሚያሳድግ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ከተማ የተገነባውን የብራውን ፉድ የበቆሎ፣ ብቅልና አልሚ ምግብ ማምረቻ ፋብሪካን መርቀው ከፍተዋል።
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት፤ የብራውን ፉድ ፋብሪካ የግብርና ምርቶችን ውጤታማነት በማሳደግ የኢንዱስትሪ ሽግግርን የሚያሳልጥ ነው።
የበለጸገ የምግብ አቅርቦትን በማሻሻል በአዕምሮና የአካል ዕድገት ጥራት ያለው ማህበረሰብ ለመገንባት ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።
በሁሉም የኢንዱስትሪ የልማት አቅጣጫዎች የተነደፉ ትልሞችን አሰናስሎ የያዘ ፋብሪካ መሆኑንም ገልጸዋል።
በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መስክም ፍትሕዊ የመሰረተ ልማት ሥርጭትን በማስፋት የዜጎችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ መሆኑን አንስተዋል።
የበቆሎ ምርትን በግብዓትነት የሚጠቀመው ፋብሪካው አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ተወዳዳሪነትን በማሳደግ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንደሚኖረው አስረድተዋል።
በስራ ዕድል ፈጠራና ፍትሃዊ የኢንቨስትመንት ሥርጭትን በማስፋት ለዘላቂ የኢኮኖሚ ግንባታ ወሳኝ መሠረት መሆኑን አንስተዋል።
ፋብሪካው የሚጠቀመው ግብዓትም በእሴት ሰንሰለት የአርሶ አደሩን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት እንደሚያረጋግጥ አስረድተዋል።
የክልሉን አምራች ኢንዱስትሪ ተጠቃሚነት በማሳደግ ከውጭ የሚገቡ የምግብ ምርቶችን በመተካት አይነተኛ ሚና እንደሚኖረውም ገልጸዋል።
የአማራ ክልል በአምራች ኢንዱስትሪ፣ ማዕድን፣ በግብርና እና ሌሎች መስኮች የመልማት ዕምቅ አቅም እንዳለው በተግባርም ሆነ በጥናት መረጋገጡን አውስተዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026