🔇Unmute
ሰቆጣ ፤ ሕዳር 13/2018 (ኢዜአ)፡- የመስኖ ልማት አቅምን በአግባቡ በመጠቀም ምርታማነትን የማሳደግና ከተረጅነት የመውጣት ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ግብርና መምሪያ አስታወቀ።
በኢትዮጵያ ያሉ እምቅ ሃብቶችን በማልማትና ብዝሃ መር የኢኮኖሚ ልማትን በመከተል ከተረጅነት ወደ አምራችነት የመሸጋገር ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል።
በተለይም ለድርቅ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን በመለየት የምርት አማራጮችን የማስፋትና ምርታማነትን ማሳደግ ላይ ትኩረት ተደርጎ በመሰራት ላይ ይገኛል።

የዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ግብርና መምሪያ የመስኖ ልማት አጠቃቀም ቡድን መሪ አቶ ደሳለኝ አዳነ፤ የመስኖ ልማትን በማጠናከር መሬት ፆም ማደር የለበትም በሚል መርህ የተቀናጀ ጥረት እየተደረገ መሆኑን ለኢዜአ ገልጸዋል።

በአካባቢው የመስኖ ልማት አቅምን በአግባቡ በመጠቀም ምርታማነትን የማሳደግና ከተረጅነት የመውጣት ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም ተናግረዋል።
በዚህም መሰረት በዘንድሮው የበጋ መስኖ 4 ሺህ 738 ሄክታር መሬት ለማልማት ታቅዶ እስካሁን ከግማሽ በላይ ማሳካት ስለመቻሉ አንስተዋል።
በአካባቢው በመስኖ ልማት እየተሳተፉ ያሉ አርሶ አደሮችም በባለሙያዎች ድጋፍና የግብአት አቅርቦት በመታገዝ የተሻለ ምርት ለማግኘት እየሰራን ነው ብለዋል።
በተለይም የሰብል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ እንዲሁም ቶሎ የሚደርሱ ሰብሎችን በመዝራት በበጋው ምርት በማግኘት ከችግር ለመውጣት የሚያስችል እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑንም ተናግረዋል።

በብሄረሰብ አስተዳደሩ በአበርገሌ ወረዳ ግብርና ፅህፈት ቤት ሃላፊ ወይዘሮ መሰረት ወልደየስ፤ በወረዳው በ1ኛ እና ሁለተኛ ዙር የተለያዩ ሰብሎችን በመስኖ ለማልማት እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው እስካሁን የልማት ስራው በስኬት መቀጠሉን ገልጸዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026