🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ሕዳር 16/2018 (ኢዜአ)፦የኢትዮጵያ ቡና እና ሻይ ባለስልጣን የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም የእውቅና መርኃ ግብር ተካሂዷል።
በመርኃ ግብሩ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ፣ የፌደራልና የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ ቡና አምራቾችና ላኪዎች የተገኙ ሲሆን በቡና ወጪ ንግድ የላቀ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ላኪዎች እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር መንግሥት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ማድረጉ የቡና ዘርፉን በከፍተኛ ሁኔታ አነቃቅቷል ብለዋል።
ከአራት ዓመታት ወዲህ በቡና ወጪ ንግድ እየተመዘገበ ያለው ከፍተኛ ስኬት የቡና አምራች ዜጎችን ተስፋ እያለመለመ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በ2017 በጀት ዓመትም የተመዘገበው የቡና ወጪ ንግድ ስኬት መግሥት ከምርት እስከ ገበያ በወሰዳቸው እርምጃዎች በአርሶ አደሮችና በዘርፉ ባለድርሻ አካላት ትጋት የተገኘ ስኬት ነው ብለዋል።
በቀጣይ የቡና ሜካናይዝድ እርሻን ማስፋትና ቡና ላይ እሴት ተጨምሮ መላክ የትኩረት ማዕከል መሆኑን ገልጸዋል።
የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር የገበያ መዳረሻዎችን እያሰፋ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፥ ቀጣይነት ያለው ፕሮሞሽንና የገበያ መዳረሻ የማስፋት ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አዱኛ ደበላ(ዶ/ር)፥ ኢትዮጵያ ልዩ ጣዕም ያላቸው የቡና ዝርያዎች ባለቤት መሆኗን አውስተዋል።
ከለውጡ ወዲህ የኢትዮጵያ ቡና በዓለም ገበያ ተፈላጊነቱ መጨመሩን ጠቅሰው፥ በ2017 በጀት ዓመት 470 ሺህ ቶን ቡና በመላክ 2 ነጥብ 65 ቢሊዮን ዶላር ገቢ በማግኘት ታሪካዊ ስኬት ተመዝግቧል ብለዋል።
በዘርፉ መሠረታዊ ለውጥ በማምጣትና የቡና ምርትና ግብይት ላይ ያሉ ችግሮችን በመፍታት የተገኘ ስኬት መሆኑንም ጠቁመዋል።
ቡና የሀገር ኢኮኖሚ ዋልታነቱን እያስመሰከረ ይገኛል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፥ ጥራታቸው አስተማማኝና ተመራጭ የሆኑ የቡናና ሻይ ምርቶችን ለውጭ ገበያ የማቅረብ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026