🔇Unmute
አዲስ አበባ፤ሕዳር 16/2018 (ኢዜአ)፦በኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የአሰላ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ለበጋ መስኖ እርሻ የሚውል ከአስራ አንድ ሺህ አምስት መቶ ኩንታል በላይ የስንዴ ምርጥ ዘር ለአርሶ አደሩ እያሰራጨ መሆኑን ገለጸ።
ጽህፈት ቤቱ የአርሶ አደሩን የምርጥ ዘር ፍላጎት ለማሟላት በራሱ፣ በክላስተር የተደራጁ አርሶ አደሮች እና ሰፋፊ እርሻ ባላቸው ባለሃብቶች መሬት ላይ የተለያዩ ዝርያ ያላቸውን ምርጥ ዘሮች በማባዛት ተደራሽ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።
በዚህም ስንዴን ጨምሮ በበርካታ የሰብል ዓይነቶች እና ዝርያዎች መስራች፣ ቅድመ መስራች እና የተመሰከረለት የዘር ደረጃዎችን በማባዛት ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል።
በኢትዮጵያ ግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን የአሰላ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ ተወካይ አቶ ማንያዘዋል ለማ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ ጽህፈት ቤቱ በኢተያ ጎንዴ በራሱ እርሻ፣ በክላስተር በተደራጁ አርሶ አደሮች እና በባለሀብቶች እርሻ ላይ ዘር እያባዛ መሆኑን ተናግረዋል።

እነዚህን የዘር ዓይነቶችም አሰላ በሚገኘው የዘር ማበጠሪያ ማሽን በማዘጋጀት ለአርሶ አደሩ ተደራሽ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ለተያዘው የበጋ መስኖም 11ሺህ 519 ኩንታል የተለያዩ ዝርያ ያላቸውን የስንዴ ምርጥ ዘር ለሁሉም ክልሎች ተደራሽ በማድረግ ላይ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
እስካሁንም ከ5ሺህ ኩንታል በላይ ማሰራጨቱን ጠቁመው፤ ቀሪዎቹንም በፍጥነት በማሰራጨት ላይ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
በማሰራጨት ላይ የሚገኙ ዝርያዎች ምርታማነታቸው ከፍተኛ የሆኑና በሽታን መቋቋም የሚችሉ የሰብል ዓይነቶች መሆናቸውንም ጠቅሰዋል።

ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ ከሚያስችሉ ግብዓቶች መካከል ምርጥ ዘር በስፋት ለአርሶ አደሩ እንዲደርስ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026