🔇Unmute
ሆሳዕና፤ ሕዳር 18/2018(ኢዜአ)፦ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በምግብ ራስን በመቻል ከተረጂነት ለመወጣት እየተከናወኑ ባሉ ሥራዎች ውጤት እየተመዘገበ መሆኑን የክልሉ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ገለፀ፡፡
ኮሚሽኑ በማረቆ ልዩ ወረዳ ቢዳራ ቀበሌ በ30 ሄክታር መሬት ላይ ያለማው የደረሰ የበቆሎ ሰብልን የማሰባሰብ ሥራ ዛሬ አስጀምሯል፡፡
የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ማዕረጉ ማቲዎስ በዚህ ወቅት እንደገለጹት በክልሉ በምግብ ራስን በመቻል ከተረጂነት ለመወጣት እየተከናወኑ ባሉ ሥራዎች ተስፋ ሰጪ ውጤት እየተመዘገበ ነው፡፡
ተረጂነት ዜጎች ያላቸውን አማራጮች ተጠቅመው እንዳይሰሩ ያደርጋል ያሉት ኮሚሽነሩ በክልሉ በተረጂነት ውስጥ ከሚገኙ ዜጎች ጋር ከችግሩ እንዲወጡ የጋራ ተግባቦት መፈጠሩን ገልጸዋል።
በክልሉ የግብርና ምርታማነትን በማሳደግ በምግብ ራስን በመቻል ከተረጂነት ለመውጣት በተሰራው ሥራ ተጨባጭ ውጤት እየተገኘ መምጣቱንም ተናግረዋል፡፡

በዚህም በክልሉ በተረጂነት ውስጥ የነበሩ ከ318ሺህ 644 በላይ የማህበረሰብ ክፍሎችን የማሸጋገር ሥራ ተሰርቷል ብለዋል፡፡
ከተረጂነት የተሸጋገሩ የማህበረሰብ ክፍሎች በቤተሰብ ጥሪት የምግብ ዋስትናን እንዲያረጋግጡ ከማድረግ በተጨማሪ የድጋፍና ክትትል ሥራ በማከናወን ራሳቸውን እንዲያበቁ እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በክልሉ የሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለማከናወን የተጀመረውን ጥረት ስኬታማ ለማድረግ በበጀት ዓመቱ 1ሺህ 431 ሄክታር ማሳ በስንዴና በበቆሎ ሰብሎች መልማቱን ገልጸዋል፡፡
የሰብዓዊ ድጋፍን በራስ አቅም ለመሸፈን መንግሥት እያከናወነ ካለው ተግባር በተጨማሪ የማህበረሰቡን የእርስ በርስ መደጋገፍ እሴት በማጠናከር በዘርፉ የታለመውን ውጤት ለማምጣት በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑንም አክለዋል።

በኮሚሽኑ የአደጋ ሥጋት ምላሽ ዝግጁነት ፕሮጀክት ፅህፈት ቤት ኃላፊ ሙርሰል አማን በበኩላቸው በክልሉ ለሚከሰቱ ሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ክስተቶች በሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም ምላሽ መስጠት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።

ለዚህም በ2017 እና በተያዘው በጀት ዓመት 100 ሺህ ኩንታል የመጠባበቂያ እህል ለማከማቸትና 120 ሚሊዮን ብር የመጠባበቂያ ፈንድ ለመያዝ ግብ ተይዞ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
በማረቆ ልዩ ወረዳ ዛሬ የተጀመረው የበቆሎ ምርት ማሰባሰብ ሥራ የዚሁ አካል መሆኑንም ገልፀዋል፡፡
በታዋቂው ታይም መጽሔት (TIME Magazine) ላይ እንግሊዛዊው ጸሐፊ ጆሽ ዊልሰን “THE POWER TO UNITE AFRICA” (አፍሪካን የማስተሳሰር ኃይል)...
Sep 14, 2026
አዳማ፤ጳጉሜን1/2018(ኢዜአ)-መጪውን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በፍጆታ ምርቶች ላይ የዋጋ ንረት እንዳይከሰት ለመከላከል ትኩረት መሰጠቱን የኦሮ...
Sep 7, 2026
ጅማ ነሐሴ 27/2018 (ኢዜአ):- ከዝናብ ጥገኝነት በመላቀቅ ወደ መስኖ ልማትና ሜካናይዜሽን እየተደረገ ያለው ሽግግር፣ በኢትዮጵያ ግብርና ውስጥ አዲስ ምዕራፍ...
Sep 3, 2026
ባህር ዳር፤ ነሐሴ 21/2018(ኢዜአ)፡-በአማራ ክልል የጥጥ ልማትን በጥራትና በብዛት በማምረት ለጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማቅረብ ልዩ ትኩረት ...
Aug 28, 2026